bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Song of Solomon 4
Song of Solomon 4
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
1
ፍቅሬ ሆይ! እንዴት ውብ ነሽ! እንዴት ያማርሽ ነሽ! ዐይኖችሽ በፊትሽ መሸፈኛ ዐይነ ርግብ ውስጥ ሲታዩ እንደ ርግብ ያማሩ ናቸው፤ ጠጒርሽ ከገለዓድ ተራራ ላይ እንደሚወርድ የፍየል መንጋ ነው።
2
ጥርሶችሽ፥ በመካከላቸው ምንም መኻን ሳይኖርባቸው መንታ መንታ እንደሚወልዱ፥ ተሸልተው በውሃ እንደ ታጠቡ፥ ነጫጭ የበጎች መንጋ ደስ ያሰኛሉ።
3
ከንፈሮችሽ እንደ ቀይ ሐር ፈትል ያማሩ ናቸው፤ ስትነጋገሪም እጅግ ደስ ያሰኛሉ፤ ሁለቱ ጒንጮችሽ በፊትሽ መሸፈኛ ዐይነ ርግብ ውስጥ ሲታዩ ለሁለት የተከፈለ የሮማን ፍንካች ይመስላሉ።
4
አንገትሽ በሺህ የሚቈጠሩ የኀያላን ጋሻዎችና የጦር ዕቃዎች ተሰቅለው የሚታዩበትን፥ የጦር ምሽግ ይሆን ዘንድ የተሠራውን የዳዊትን ግንብ ይመስላል።
5
ሁለቱ ጡቶችሽ መንታ ሆነው የተወለዱና በሱፍ አበባዎች መካከል የተሰማሩ የዋልያ ግልገሎችን ይመስላሉ።
6
ሌሊቱ እስከሚነጋና ጨለማውም እስከሚያልፍ ድረስ ወደ ከርቤ ተራራና ወደ ዕጣን ኮረብታ ሄጄ ዐርፋለሁ።
7
ፍቅሬ ሆይ! ሁለንተናሽ ውብ ነው፤ ምንም እንከን የለብሽም።
8
ሙሽራዬ ሆይ! ከሊባኖስ ወደ እኔ ነይ፤ ከሊባኖስ ወደ እኔ ነይ፤ ከአማና ተራራ ጫፍ ውረጂ፤ የአንበሳና የነብር መኖሪያ ከሆኑት ከሠኒርና ከሔርሞን ተራራዎች ወርደሽ ነይ
9
ውድ እኅቴ የሆንሽ ሙሽራዬ ሆይ፥ የዐይኖችሽ አመለካከትና የአንገትሽ ድሪ ልቤን ማርኮታል፤
10
ውድ እኅቴ የሆንሽ ሙሽራዬ ሆይ፥ ፍቅርሽ እንዴት ያስደስታል! ፍቅርሽ ከወይን ጠጅ ይልቅ ደስ ያሰኛል፤ የሽቶሽ መዓዛ ከማንኛውም ሽቶ ይበልጣል።
11
ሙሽራዬ ሆይ! ከከንፈሮችሽ የማር ወለላ ይፈስሳል፤ ከአንደበትሽም ማርና ወተት ይፈልቃል፤ የልብስሽም መዓዛ እንደ ሊባኖስ ሽቱ ነው።
12
አንቺ የእኔ ሙሽራ፥ እንደ አትክልት ቦታና ለሌሎች እንደ ተዘጋ ምንጭ ነሽ።
13
የአንቺ መተላለፊያ በጣፋጭ ፍሬዎች እንደ ተሞላ እንደ ሮማን የአትክልት ቦታ ነው።
14
ናርዶስ፥ ቀጋ፥ ጠጅ ሣርና ቀረፋ፥ እንዲሁም ሽታቸው እንደ ዕጣን መዓዛ ያላቸው ልዩ ልዩ ተክሎች ይገኙባታል፤ እንዲሁም ከርቤ፥ የሬት አበባና ልዩ ልዩ የቅመማቅመም ተክሎች ይበቅሉባታል።
15
አንቺ የአትክልት ቦታን እንደምታጠጣ ምንጭ ነሽ፤ የሕይወት ውሃም እንደሚገኝባት ጒድጓድ ነሽ፤ ከሊባኖስ ተራራ ሥር እንደሚፈልቅ ወንዝ ነሽ።
16
የሰሜን ነፋስ ሆይ! ንቃ! አንተም የደቡብ ነፋስ ሆይ! ወደዚህ ና! በአትክልት ቦታዬም ላይ ንፈስ፤ ዐየሩም በመልካም ሽታ የተሞላ ይሁን፤ ውዴም ወደ አትክልት ቦታው ይምጣ፤ ምርጥ የሆኑትንም ፍሬዎች ይመገብ።
← Chapter 3
Chapter 5 →