bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Psalms 97
Psalms 97
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
1
እግዚአብሔር ንጉሥ ነው! ምድር ሆይ ደስ ይበልሽ! እናንተ በባሕር ውስጥ ያላችሁ ደሴቶች ሁሉ፥ ደስ ይበላችሁ!
2
ብሩህና ጥቊር ደመና ዙሪያውን ከበውታል፤ ጽድቅና ፍትሕ የዙፋኑ መሠረት ናቸው።
3
እሳት እፊት እፊቱ ይሄዳል፤ በዙሪያው ያሉትን ጠላቶቹን ያቃጥላል።
4
መብረቁ በዓለም ላይ ያበራል፤ ምድርም አይታ ትንቀጠቀጣለች።
5
በምድር ሁሉ ጌታ በእግዚአብሔር ፊት፥ ተራራዎች እንደ ሰም ይቀልጣሉ።
6
ሰማያት ጽድቁን ይናገራሉ፤ ሕዝቦች ሁሉ ክብሩን ያያሉ።
7
ለጣዖቶች የሚሰግዱና በእነርሱ የሚመኩ ሁሉ ያፍራሉ፤ እናንተ ሐሰተኞች አማልክት ሁሉ ለእግዚአብሔር ስገዱ።
8
አምላክ ሆይ! ስለ ትክክለኛ ፍርድህ የጽዮን ሕዝብ ደስ ይላቸዋል፤ የይሁዳ ከተሞችም ሐሤት ያደርጋሉ።
9
እግዚአብሔር ሆይ! አንተ በምድር ሁሉ ላይ ልዑል አምላክ ነህ፤ ሐሰተኞች አማልክት ሁሉ በሥልጣንህ ሥር ናቸው።
10
እግዚአብሔር ክፉ ነገርን የሚጠሉትን ሁሉ ይወዳል፤ ታማኞች አገልጋዮቹን ያድናቸዋል፤ ከክፉ መንፈስ ኀይልም እንዲያመልጡ ያደርጋቸዋል።
11
ብርሃን ለደጋግ ሰዎች፥ ደስታም ለልበ ቅኖች ይወጣላቸዋል።
12
እግዚአብሔር ስላደረገው ነገር ጻድቃን ሁሉ ደስ ይበላችሁ! ቅዱስ ስሙንም አመስግኑ!
← Chapter 96
Chapter 98 →