bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Psalms 79
Psalms 79
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
1
አምላክ ሆይ! አሕዛብ ወደ ምድርህ መጡ፤ ቤተ መቅደስህን አረከሱ፤ ኢየሩሳሌምንም አፈራረሱአት።
2
የሕዝብህን ሬሳ ለሰማይ ወፎችና የታማኞችህን ሥጋ ለአራዊት ምግብ አድርገው ሰጡ።
3
ደማቸውንም እንደ ውሃ በኢየሩሳሌምም ዙሪያ አፈሰሱ፤ የሞቱትንም የሚቀብር አንድ ሰው እንኳ አልነበረም።
4
ለጐረቤቶቻችን መዘባበቻ፥ በዙሪያችን ላሉ መሳቂያና መሳለቂያ ሆነናል።
5
እግዚአብሔር ሆይ! በእኛ ላይ የምትቈጣው እስከ መቼ ድረስ ነው? ቅናትህ እንደ እሳት ሲነድ ይኖራልን?
6
ቊጣህን አንተን በአምላክነትህ ወደማያውቁና ወደ አንተ ወደማይጸልዩ ሕዝቦችና መንግሥታት ላይ መልስ።
7
ይህንንም የምታደርገው እነርሱ ሕዝቦችህን ስለ ገደሉና ርስታቸውን ስለ አወደሙ ነው።
8
እኛ በጣም ስለ ተዋረድን በአባቶቻችን ኃጢአት ምክንያት አትቅጣን ፈጥነህም ምሕረት አድርግልን።
9
አዳኛችን አምላክ ሆይ! እርዳን፤ ስለ ራስህ ክብር ስትል ተቤዠን፤ ኃጢአታችንንም ይቅር በልልን።
10
ለምን አሕዛብ “አምላካቸው የት አለ?” ብለው ይጠይቁ? የፈሰሰውን የአገልጋዮችህን ደም እንደምትበቀል በፊታችን ለአሕዛብ አሳውቅ።
11
የእስረኞች መቃተት ወደ አንተ እንዲደርስ አድርግ፤ ሞት የተፈረደባቸውንም በታላቁ ኀይልህ አድናቸው።
12
ጌታ ሆይ! ጐረቤቶቻችን በአንተ ላይ ስለ ተዘባበቱ በሰባት እጥፍ ተበቀላቸው።
13
በዚያን ጊዜ የመንጋህ በጎች የሆንን ሕዝቦችህ ለዘለዓለም እናመሰግንሃለን፤ ለተከታዩ ትውልድ ሁሉ ምስጋናህን እንናገራለን።
← Chapter 78
Chapter 80 →