bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Psalms 73
Psalms 73
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
1
ልባቸው ንጹሕ ለሆነ እስራኤላውያን እግዚአብሔር ቸር ነው።
2
በእኔ በኩል ግን እርምጃዎቼ እየተንገዳገዱ፥ እግሮቼም ሊንሸራተቱ ተቃርበዋል።
3
ይህም የሆነው ትዕቢተኞችና ክፉዎች ሰዎች ሲበለጽጉ በማየቴ ቅናት አድሮብኝ ነው።
4
እነርሱም ምንም ሕመም ስለሌለባቸው፥ ሰውነታቸው ጤናማና ወዛም ነው።
5
እንደ ሌሎች ሰዎች አይጨነቁም፤ በሌሎች ላይ የሚደርሰው ሥቃይ በእነርሱ ላይ አይደርስም።
6
ስለዚህ ትዕቢትን እንደ ድሪ አጥልቀዋል፤ ዐመፅንም እንደ ልብስ ለብሰዋል።
7
አእምሮአቸው ክፉ ሐሳብን እያፈለቀ ከዐይነ ስባቸው የሚወጡት ዐይኖቻቸው አፍጥጠው ይመለከታሉ።
8
በሌሎች ሰዎች ላይ እያፌዙ የተንኰል ንግግርን ይናገራሉ፤ በትዕቢታቸውም የመጨቈን ዛቻን ይዝታሉ።
9
በእግዚአብሔር ላይ መናገርን ይዳፈራሉ፤ በምድር ላይ ከመናገርም አያቆሙም።
10
የእግዚአብሔር ሰዎች እንኳ ሳይቀሩ ወደ እነርሱ ያዘነብላሉ፤ የሚነግሩአቸውንም ሁሉ ይቀበላሉ።
11
እነርሱም “በውኑ እግዚአብሔር ያውቃልን? ልዑል እግዚአብሔርስ ዕውቀት አለውን?” ይላሉ።
12
እንግዲህ ክፉዎች እንደዚህ ናቸው፤ ሁልጊዜ እንደ ተዝናኑ ናቸው። ዘወትርም ተጨማሪ ሀብት ያገኛሉ።
13
ሐሳቤን በቅንነት መጠበቄና በደልንም ከመሥራት መቈጠቤ ምን ጠቀመኝ?
14
ቀኑን ሙሉ ተሠቃየሁ፤ በየማለዳውም ተቀጣሁ።
15
እነርሱ እንደሚናገሩት ለመናገር ባስብ ኖሮ ለሕዝብህ ታማኝ ባልሆንኩም ነበር፤
16
ይህን ለመረዳት ኅሊናዬን አነቃሁ፤ ነገር ግን በጣም አስቸጋሪ ሆኖ አገኘሁት።
17
ወደ መቅደስህ እስክገባ ድረስ ምንም ማወቅ አልቻልኩም፤ ወደ መቅደስህ በገባሁ ጊዜ ግን በክፉዎች ላይ ምን እንደሚደርስባቸው ተረዳሁ።
18
በሚያዳልጥ ስፍራ ታኖራቸዋለህ፤ ወድቀው እንዲጠፉም ታደርጋቸዋለህ።
19
በቅጽበት ተደመሰሱ፤ መጨረሻቸውም አስደንጋጭ ሆነ።
20
እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ስትነሣ እነርሱ በማለዳ እንደሚረሳ ሕልም ይጠፋሉ።
21
ኅሊናዬን በጣም መረረው፤ ልቤም ተሰበረ።
22
ጌታ ሆይ! እኔ ለአንተ ከእንስሶች የማልሻል፥ ምንም የማይገባኝ አላዋቂ ነበርኩ።
23
ነገር ግን ዘወትር ከአንተ ጋር እኖራለሁ፤ አንተም ቀኝ እጄን ትይዛለህ።
24
በምክርህ ትመራኛለህ፤ በመጨረሻም በክብር ትቀበለኛለህ።
25
በሰማይ ከአንተ ሌላ ማን አለኝ? በምድርስ አንተን ካገኘሁ ሌላ ምን እሻለሁ?
26
አእምሮዬና ጒልበቴ ሊደክሙ ይችላሉ፤ እግዚአብሔር ግን እስከ ዘለዓለም ብርታቴና አለኝታዬ ነው።
27
እነሆ፥ ከአንተ የሚርቁ ይጠፋሉ፤ አንተን የሚክዱህን ሁሉ ትደመስሳቸዋለህ።
28
ለእኔ ግን ወደ እግዚአብሔር መቅረቤ መልካም ነው፤ የአንተን ሥራ ሁሉ ለማብሠር እንድችል አንተን ጌታ አምላኬን መጠጊያዬ አድርጌአለሁ።
← Chapter 72
Chapter 74 →