bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Psalms 71
Psalms 71
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
1
እግዚአብሔር ሆይ! እንድትጠብቀኝ ወደ አንተ ስለ መጣሁ ኀፍረት እንዲደርስብኝ አታድርግ!
2
በጽድቅህ ከችግር እንዳመልጥ አድርገህ አውጣኝ አድምጠህም አድነኝ።
3
በምሄድበት ቦታ ሁልጊዜ አንተ ኀያል አምባዬ ሁን፤ አንተ ኀያል አምባዬና ምሽጌ ስለ ሆንክ በትእዛዝህ አድነኝ።
4
አምላኬ ሆይ! ከክፉ ኀይልና ርኅራኄ ከሌለው ዐመፀኛ እጅ አድነኝ።
5
ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! ተስፋዬን በአንተ ላይ አደርጋለሁ፤ ከልጅነቴ ጀምሮ መታመኛዬ አንተ ነህ።
6
በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በአንተ ላይ እታመናለሁ፤ ከእናቴ ማሕፀን እንድወለድ ያደረግኸኝ አንተ ነህ፤ እኔም ዘወትር አመሰግንሃለሁ።
7
አንተ ብርቱ ተከላካይ ስለ ሆንክልኝ ሕይወቴ ለብዙዎች ምሳሌ ሆኖአል።
8
አንደበቴ በአንተ ምስጋና የተሞላ ነው፤ ስለ ክብርህም ቀኑን ሙሉ እናገራለሁ። ድምፄንም ከፍ አድርጌ ለአንተ ምስጋና አቀርባለሁ።
9
አሁንም በእርጅናዬ ዘመን አትጣለኝ፤ ደካማ በምሆንበትም ጊዜ አትተወኝ።
10
ጠላቶቼ በእኔ ላይ ክፉ ነገር ይመክራሉ፤ ሊገድሉኝ የሚፈልጉትም በእኔ ላይ ያሤራሉ።
11
“እግዚአብሔር ትቶታል፤ ተከታትለን እንያዘው፤ የሚያድነው ማንም የለም” ይላሉ።
12
አምላክ ሆይ! ከእኔ አትራቅ፤ አምላክ ሆይ! ፈጥነህ እርዳኝ።
13
ተቃዋሚዎቼ ይፈሩ፤ ይጥፉም፤ ሊጐዱኝ የሚፈልጉ ይናቁ፤ ይዋረዱም።
14
እኔ ግን ዘወትር አንተን ተስፋ አደርጋለሁ፤ በበለጠም መላልሼ አመሰግንሃለሁ።
15
ምንም እንኳ ማስተዋል ቢያዳግተኝ፥ አንደበቴ ስለ ትክክለኛ ፍርድህና ስለ አዳኝነትህ ቀኑን ሙሉ ይናገራል።
16
ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! መጥቼ ኀያል ሥራዎችህን ዐውጃለሁ፤ ትክክለኛ ፍርድ የመስጠት ኀይል የአንተ ብቻ መሆኑን እናገራለሁ፤
17
አምላክ ሆይ! አንተ ከልጅነቴ ጀምረህ አስተማርከኝ፤ ገና አሁንም ድንቅ ሥራህን እናገራለሁ።
18
አምላክ ሆይ! ሥልጣንህን ለሚመጣው ትውልድ፥ ኀይልህንም ለሚመጡት ሁሉ እስክገልጥና አርጅቼ እስክሸብት ድረስ እንኳ አትተወኝ።
19
አምላክ ሆይ! ጽድቅህ እስከ ሰማይ ይደርሳል፤ ታላላቅ ነገሮችን አድርገሃል፤ አምላክ ሆይ! አንተን የሚመስል ማን ነው?
20
በብዙ ችግርና መከራ እንድሠቃይ አድርገኸኛል፤ ሆኖም እንደገና ከመሬቱ ጥልቅ ጒድጓድ አውጥተህ አዲስ ሕይወትን ትሰጠኛለህ።
21
ክብሬን ታሳድጋለህ፤ እንደገናም ታጽናናኛለህ።
22
አምላኬ፥ የእስራኤል ቅዱስ ሆይ! ስለ ታማኝነትህ በበገና አመሰግንሃለሁ፤ በመሰንቆም የምስጋና መዝሙር አቀርብልሃለሁ።
23
ያዳንከኝ እኔ የምስጋና መዝሙር ስዘምርልህ። ከንፈሮቼ የደስታ ጩኸት ይጮኻሉ።
24
ሊጐዱኝ የሚፈልጉ ስላፈሩና ግራ ስለ ተጋቡ አንደበቴ ቀኑን ሙሉ ስለ እውነተኛ ርዳታህ ይናገራል።
← Chapter 70
Chapter 72 →