bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Psalms 59
Psalms 59
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
1
አምላክ ሆይ! ከጠላቶቼ አድነኝ፤ በእኔ ላይ ከሚነሡ ሰዎችም ጠብቀኝ።
2
ከነዚያ ከክፉ ሰዎች አድነኝ፤ ከነዚያም ነፍሰ ገዳዮች ታደገኝ።
3
እንዴት እንደ ሸመቁብኝ ተመልከት! እግዚአብሔር ሆይ! ምንም በደልና ኃጢአት ሳልሠራ ዐመፀኞች ሰዎች በእኔ ላይ ያሤራሉ።
4
ምንም በደል ሳልሠራ ሊያጠቁኝ ተዘጋጅተዋል፤ ይህን ተመልከትና ተነሥተህ እርዳኝ።
5
አንተ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የእስራኤል አምላክ ነህ፤ ሕዝቦችን ለመቅጣት ተነሥ፤ ክፉ ከዳተኞችን ያለ ምሕረት ቅጣቸው።
6
እነርሱ በከተማይቱ ውስጥ እንደ ውሻ እያላዘኑ ሲልከሰከሱ ውለው ወደ ማታ ይመለሳሉ።
7
ከአፋቸው የሚወጣውን ተመልከት፤ ምላሳቸው እንደ ተሳለ ሰይፍ ነው፤ ነገር ግን ማንም የሚሰማቸው አይመስላቸውም።
8
እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ግን በእነርሱ ላይ ትስቃለህ፤ አሕዛብን ሁሉ ትንቃለህ።
9
አምላክ ሆይ! መጠጊያዬ ስለ ሆንክ በአንተ እተማመናለሁ።
10
አምላኬ በዘለዓለማዊ ፍቅሩ በፊቴ ይሄዳል፤ ጌታዬ፥ ጠላቶቼን በንቀት ዐይን እንድመለከታቸው ያደርገኛል።
11
መከታችን እግዚአብሔር ሆይ! ወገኖቼ የአንተን ተበቃይነት እንዳይረሱ፥ አትግደላቸው፤ ነገር ግን በኀይልህ በትናቸው፤ አዋርዳቸውም።
12
ከአንደበታቸው ኃጢአት አይጠፋም፤ ንግግራቸው ሁሉ ኃጢአት የሞላበት ነው፤ እነርሱ ስለሚራገሙና ስለሚዋሹ በትዕቢታቸው ይያዙ!
13
በቊጣህ አጥፋቸው፤ ፈጽመህም ደምስሳቸው፤ በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር እስራኤልን እንደሚያስተዳድርና ግዛቱም በምድር ሁሉ እንደ ተንሰራፋ፥ ሰው ሁሉ ያውቃል።
14
ጠላቶቼ በከተማይቱ ውስጥ እንደ ውሻ እያላዘኑ ሲልከሰከሱ ውለው፥ ወደ ማታ ይመለሳሉ።
15
እነርሱ ምግብ ለማግኘት እንደሚቅበዘበዙና በቂ ምግብ ካላገኙም እንደሚያላዝኑ ውሾች ናቸው።
16
በመከራዬ ቀን መጠጊያዬና ምሽጌ ስለ ሆንክ ስለ ኀያልነትህ ክብርና ስለ ዘለዓለማዊ ፍቅርህ ዘወትር በማለዳ እዘምራለሁ።
17
አምላክ ሆይ! አንተ ብርታቴ ነህ፤ አንተ መጠጊያዬ ነህ፤ ዘለዓለማዊ ፍቅርህንም ታሳየኛለህ፤ ስለዚህ የምስጋና መዝሙር አቀርብልሃለሁ።
← Chapter 58
Chapter 60 →