bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Psalms 51
Psalms 51
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
1
አምላክ ሆይ! ስለ ዘለዓለማዊ ፍቅርህ ይቅር በለኝ፤ ስለ ታላቁ ምሕረትህም ኃጢአቴን ደምስስልኝ።
2
በደሌን ሁሉ አጥበህ አስወግድልኝ፤ ከኃጢአቴም አንጻኝ።
3
እኔ ስሕተቴን ዐውቃለሁ፤ የኃጢአቴንም ብዛት ዘወትር እገነዘባለሁ።
4
እኔ ያመፅኩት በአንተ ላይ ነው፤ የበደልኩትም አንተን ብቻ ነው፤ አንተ የምትጠላውን ነገር አደረግሁ፤ ስለዚህ በእኔ ላይ መፍረድህና እኔንም መቅጣትህ ትክክል ነው።
5
ከተፀነስኩበት ጊዜ ጀምሮ ኀጢአተኛ ነኝ፤ ከተወለድኩበትም ጊዜ ጀምሮ በደለኛ ነኝ።
6
አንተ ቅንነትንና እውነትን ስለምትወድ የጥበብህን ምሥጢር አስተምረኝ።
7
በሂሶጵ ቅጠል ረጭተህ ኃጢአቴን አስወግድልኝ፤ እኔም እነጻለሁ። እጠበኝ፤ እኔም ከበረዶ ይበልጥ ነጭ እሆናለሁ።
8
የሰበርካቸውን አጥንቶቼን አድሰህ የደስታንና የሐሤትን ድምፅ አሰማኝ፤
9
ፊትህን ከኃጢአቴ መልስ፤ በደሌን ሁሉ ደምስስ።
10
አምላክ ሆይ! ንጹሕ ልብን ፍጠርልኝ፤ አዲስና የጸና መንፈስን ስጠኝ።
11
ከፊትህ አታርቀኝ፤ ቅዱስ መንፈስህንም ከእኔ አትውሰድብኝ።
12
በአዳንኸኝ ጊዜ እንደ ሰጠኸኝ ዐይነቱን ደስታ ስጠኝ፤ ታዛዥ እንድሆን አድርገኝ
13
ከዚህ በኋላ ትእዛዝህን ለሕግ ተላላፊዎች አስተምራለሁ፤ ኃጢአተኞችም ወደ አንተ ይመለሳሉ።
14
አቤቱ አዳኜ አምላኬ ሆይ! ደም ከማፍሰስ አድነኝ፤ ስለ አዳኝነትህም የምስጋና መዝሙር እዘምራለሁ።
15
እግዚአብሔር ሆይ! እንድናገር እርዳኝ፤ እኔም አመሰግንሃለሁ።
16
መሥዋዕት አያስደስትህም እንጂ ባቀረብኩልህ ነበር፤ የሚቃጠል መሥዋዕትም አያስደስትህም።
17
ለእግዚአብሔር የሚቀርብ መሥዋዕት የተሰበረ ልብ ነው፤ እግዚአብሔር ሆይ አንተ የተሰበረውንና የተዋረደውን ልብ አትንቅም።
18
አምላክ ሆይ! ጽዮንን ለመርዳት፥ የኢየሩሳሌምን ቅጥሮች ለመገንባት እባክህ ፈቃድህ ይሁን።
19
በዚያን ጊዜ በትክክለኛ መሥዋዕትና በሚቃጠል መሥዋዕት ትደሰታለህ፤ እኛም በመሠዊያህ ላይ እንደገና ኰርማዎችን እናቀርባለን።
← Chapter 50
Chapter 52 →