bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Psalms 48
Psalms 48
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
1
እግዚአብሔር ታላቅ ስለ ሆነ በአምላካችን ከተማ፤ በተቀደሰ ተራራው ላይ ከፍ ያለ ምስጋና ሊቀርብለት ይገባዋል።
2
በሰሜን በኩል የምትገኘው፥ በከፍታዋና በውበትዋ የምትደነቀው፥ የጽዮን ተራራ የታላቁ ንጉሥ ከተማ ነች፤ እርስዋም በምድር ላሉ ሁሉ ደስታን ታጐናጽፋለች።
3
እግዚአብሔር በምሽግዋ ውስጥ ነው፤ እርሱም ከለላዋ መሆኑን አስመስክሮአል።
4
ከተማይቱን ለማጥቃት ነገሥታት ኀይላቸውን አሰባሰቡ።
5
ነገር ግን ባዩአት ጊዜ ደነገጡ፤ ፈርተውም ሸሹ።
6
እዚያም ሳሉ በፍርሃት ተርበደበዱ፤ ምጥ እንደ ያዛትም ሴት ተጨነቁ።
7
በምሥራቅ ነፋስ እንደሚሰባበሩ የተርሴስ መርከቦች ሆኑ።
8
እግዚአብሔር ያደረገውን ሰምተናል፤ አሁንም ሁሉን ቻይ ጌታ የራሱ በሆነችው ከተማ ያደረገውን በዐይናችን አየን፤ እርሱ ከተማይቱን ለዘለዓለም ጸንታ እንድትኖር ያደርጋታል።
9
አምላክ ሆይ! በመቅደስህ ውስጥ ስለ ዘለዓለማዊው ፍቅርህ እናስባለን።
10
አምላክ ሆይ! ምስጋናህ እስከ ዓለም ዳርቻ እንደ ደረሰ ስምህም እንደዚሁ ገናና ነው።
11
ፍርድህ ትክክለኛ ስለ ሆነ በጽዮን የሚኖሩ ሕዝቦች ደስ ይላቸዋል፤ በይሁዳ ከተሞች የሚኖሩ ሁሉ ሐሴት ያደርጋሉ።
12
ተሰልፋችሁ ጽዮንን ዙሩአት፤ ማማዎችዋንም ቊጠሩ።
13
ለሚመጣው ትውልድ ታስተላልፉ ዘንድ ጠንካራ ቅጥሮችዋን አስተውሉ፤ ምሽጎችዋንም ተመልከቱ።
14
የምትነግሩአቸውም “እግዚአብሔር እንዲህ ነው፤ አምላካችን ዘለዓለማዊ ነው፤ ወደፊትም ለዘለዓለም ይመራናል” ብላችሁ ነው።
← Chapter 47
Chapter 49 →