bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Psalms 45
Psalms 45
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
1
ልቤ መልካም ርእስን ያፈልቃል፤ ጽሑፌም የሚያተኲረው በንጉሡ ላይ ነው፤ አንደበቴም እንደ መልካም ጸሐፊ ብዕር ነው።
2
አንተ ከሰዎች ሁሉ ይልቅ እጅግ የተዋብክ ነህ፤ ንግግርህም ሞገስ የሞላበት ነው፤ እግዚአብሔር ለዘለዓለም ባርኮሃል።
3
በክብርና በግርማ የተሞላህ ኀያል ንጉሥ ሆይ፥ ሰይፍህን ታጠቅ።
4
ስለ እውነትና ስለ ፍትሕ ግርማን ተጐናጽፈህ ድል ለማድረግ ገሥግሥ፤ ኀይልህም ታላላቅ ድሎችን ያስገኛል።
5
ፍላጻዎችህ የተሳሉ ናቸው፤ የጠላቶችህንም ልብ ይወጋሉ፤ መንግሥታትም ተሸንፈው በእግርህ ሥር ይወድቃሉ።
6
አምላክ ሆይ! ዙፋንህ ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም የጸና ነው። በትረ መንግሥትህም የፍትሕ በትረ መንግሥት ነው።
7
አንተ መልካሙን ነገር ትወዳለህ፤ ክፉውን ነገር ትጠላለህ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክህ መረጠህ፤ ከሌሎች ነገሥታትም ይበልጥ የደስታን ዘይት ቀባህ።
8
ከከርቤ፥ ከእሬትና ከብርጒድ የተቀመመ ሽቶ በንጉሣዊ ልብስህ ላይ ተርከፍክፎአል፤ በዝሆን ጥርስ በተጌጠው ቤተ መንግሥትህም የበገና ሙዚቃ ቃና ያስደስትሃል።
9
በቤተ መንግሥትህ ከሚገኙት ወይዛዝርት መካከል፥ የነገሥታት ሴቶች ልጆች ይገኛሉ፤ ንግሥቲቱም በንጹሕ ወርቅ ያሸበረቀ ጌጠኛ ልብስ ተጐናጽፋ ከዙፋንህ በስተቀኝ ቆማለች።
10
አንቺ ልጄ ሆይ! የምልሽን ስሚ፤ ቃሌንም አድምጪ፤ ሕዝብሽንና የአባትሽን ቤት እርሺ።
11
በውበትሽ ንጉሡ ይወድሻል፤ ሆኖም ጌታሽ በመሆኑ እጅ በመንሣት አክብሪው።
12
የጢሮስ ሰዎች ስጦታ ያመጡልሻል፤ ሀብታሞችም ደጅ ይጠኑሻል።
13
በቤተ መንግሥት የተቀመጠችው ልዕልት አጊጣለች ልብስዋም በወርቅ አሸብርቆአል።
14
ጌጠኛ ልብስዋንም ተጐናጽፋ ወደ ንጉሡ ትቀርባለች፤ ሚዜዎችዋ የሆኑ ልጃገረዶችም ያጅቡአታል፤
15
በደስታና በሐሤትም አብረው ወደ ንጉሡ ቤት ይገባሉ።
16
ንጉሥ ሆይ! በቀድሞ አባቶችህ ተተክተው የሚነግሡ ብዙ ልጆች ይኖሩሃል፤ አንተም በምድር ሁሉ ላይ ልዑላን አድርገህ ትሾማቸዋለህ።
17
እኔ በየትውልዱ ዝናህን እገልጣለሁ፤ ስለዚህ ሕዝቦች ሁሉ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ያመሰግኑሃል።
← Chapter 44
Chapter 46 →