bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Psalms 34
Psalms 34
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
1
ዘወትር እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፤ ምስጋናውም ዘወትር በአንደበቴ ነው።
2
በሙሉ ልቤ በእግዚአብሔር እመካለሁ፤ ትሑቶች ይህን ሰምተው ደስ ይበላቸው!
3
የእግዚአብሔርን ታላቅነት ከእኔ ጋር አስታውቁ፤ በኅብረትም ስሙን እናክብር።
4
የእግዚአብሔርን ርዳታ ፈለግኹ እርሱም ሰማኝ፤ ከምፈራውም ነገር ሁሉ አዳነኝ።
5
ወደ እርሱ የሚመለከቱ ሁሉ ፊታቸው ይበራል፤ ፊታቸውም ከቶ በኀፍረት አይሸፈነም።
6
ይህ ድኻ ሰው ተጣራ፤ እግዚአብሔርም ሰማው፤ ከችግሩም ሁሉ አዳነው።
7
የእግዚአብሔር መልአክ እግዚአብሔርን የሚፈሩትን ሰዎች ይጠብቃል፤ በዙሪያቸውም ሆኖ ከአደጋ ያድናቸዋል።
8
የእግዚአብሔርን ደግነት እዩና ቅመሱ፤ እርሱን ከለላ ያደረገ የተባረከ ነው።
9
እርሱን የሚፈሩት ሁሉ ምንም ስለማያጡ እናንተ ቅዱሳኑ እግዚአብሔርን ፍሩ
10
የአንበሳ ደቦሎች ያጣሉ፤ ይራባሉም፤ እግዚአብሔርን የሚፈልጉት ግን ምንም አይጐድልባቸውም፤ መልካም ነገርም አያጡም።
11
ልጆቼ ሆይ! ኑ አድምጡኝ፤ እኔም እግዚአብሔርን መፍራት አስተምራችኋለሁ።
12
ከእናንተ መኖርንና ለብዙ ዘመንም መልካም ነገርን ለማየት የሚመኝ ማነው?
13
እንግዲያውስ መጥፎ ነገር ከማውራትና ሐሰት ከመናገር ተቈጠቡ።
14
ከክፉ ነገር ሽሹ፤ መልካም ነገርንም አድርጉ፤ ሰላምን ፈልጉአት፤ ተከተሉአትም።
15
እግዚአብሔር ወደ ጻድቃን ይመለከታል፤ ጸሎታቸውንም ያደምጣል።
16
ክፉ አድራጊዎችን ግን ይቃወማል፤ መታሰቢያቸውንም ከምድር ላይ ያጠፋል።
17
ጻድቃን ወደ እግዚአብሔር ይጮኻሉ፤ እርሱም ይሰማቸዋል፤ ከችግራቸውም ሁሉ ያድናቸዋል።
18
ልባቸው ለተሰበረ እግዚአብሔር ቅርብ ነው፤ መንፈሳቸው የደቀቀውንም ያድናቸዋል።
19
ጻድቅ ብዙ መከራ ይደርስበታል፤ እግዚአብሔር ግን ከዚህ ሁሉ ያድነዋል።
20
እግዚአብሔር አጥንቶቹን ስለሚጠብቅ ከእነርሱ አንዱ እንኳ አይሰበርም።
21
ክፋት ክፉ ሰዎችን ይገድላል፤ ደጋግ ሰዎችን የሚጠሉ ሁሉ ይቀጣሉ።
22
እግዚአብሔር የአገልጋዮቹን ሕይወት ያድናል፤ በእርሱ የተማጠኑትም ክፉ ነገር አይደርስባቸውም።
← Chapter 33
Chapter 35 →