bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Psalms 31
Psalms 31
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
1
እግዚአብሔር ሆይ! መጠጊያ እንድትሆነኝ ወደ አንተ መጥቻለሁ፤ ስለዚህ እንዳፍር አታድርገኝ፤ በጽድቅህም አድነኝ።
2
ጌታ ሆይ! አድምጠኝ፤ ፈጥነህም በመምጣት አድነኝ፤ መጠጊያ አለትና ጠንካራ ምሽግ ሆነህ አድነኝ።
3
አንተ መጠጊያ ምሽጌ ነህ፤ ስለ ስምህ ስትል ምራኝ፤ የምሄድበትንም መንገድ አሳየኝ።
4
አንተ መጠጊያዬ ስለ ሆንክ ጠላቶቼ ከዘረጉብኝ ወጥመድ አውጣኝ።
5
የእውነት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! ነፍሴን ለአንተ እሰጣለሁና አድነኝ።
6
ዋጋቢሶች ለሆኑ ጣዖቶች የሚሰግዱትን ሁሉ ትጠላለህ፤ እኔ ግን በአንተ እታመናለሁ።
7
ስለ ዘለዓለማዊ ፍቅርህ ደስ ይለኛል፤ ሐሴትም አደርጋለሁ፤ መከራዬን አይተህ ጭንቀቴን ታውቃለህ፤
8
ለጠላቶች አሳልፈህ አልሰጠኸኝም፤ ነገር ግን ሰፊ መንገድ ከፈትክልኝ።
9
እግዚአብሔር ሆይ! በችግር ላይ ስለ ሆንኩ ምሕረትን አድርግልኝ፤ ዐይኖቼ፥ ነፍሴና ሥጋዬ በሐዘን ደክመዋል።
10
ሕይወቴ በሐዘን ዕድሜዬም በመቃተት አለቀ፤ በችግሬ ምክንያት ኀይል አጣሁ፤ አጥንቶቼም ደከሙ።
11
እኔ የጠላቶቼ መሳለቂያ፥ ለጐረቤቶቼ አስደንጋጭ፥ ለሚያውቁኝም አስፈሪ ነኝ፤ በመንገድ ሲያዩኝም ከእኔ ይሸሻሉ።
12
እንደ ሞተ ሰው ተረሳሁ፤ ተሰብሮ እንደ ተጣለ የሸክላ ዕቃ ሆንኩ።
13
የብዙ ሰዎችን ሹክሹክታ እሰማለሁ፤ በሁሉም አቅጣጫ ፍርሀት አለ፤ በእኔ ላይ ያሤራሉ፤ ሊገድሉኝ በማቀድ ያድማሉ።
14
እግዚአብሔር ሆይ! አንተ አምላኬ ነህ፤ እኔ በአንተ እታመናለሁ።
15
እኔ ሁልጊዜ በአንተ እጅ ነኝ፤ ከጠላቶቼ እጅና ከሚያሳድዱኝ ሁሉ አድነኝ።
16
ወደ አገልጋይህ በፈገግታ ተመልከት፤ በዘለዓለማዊ ፍቅርህም አድነኝ።
17
እግዚአብሔር ሆይ! ወደ አንተ በምጣራበት ጊዜ አታሳፍረኝ፤ ክፉዎች ግን ይፈሩ፤ ጸጥ ብለውም ወደ ሲኦል ይውረዱ።
18
በጻድቅ ላይ በትዕቢትና በንቀት በኩራትም ስለሚናገር የሐሰት አንደበታቸውን ጸጥ አሰኝ።
19
በአንተ ለመከለል ወደ አንተ ለሚጠጉ በሰዎች ሁሉ ፊት የምትሰጠው ለሚፈሩህ ያዘጋጀኸው ደግነት ምንኛ ትልቅ ነው!
20
ከሚያሤሩባቸው ሰዎች በመኖሪያህ ጥላ ሥር ትደብቃቸዋለህ፤ ከመርዘኛ አንደበትም በከለላህ ትጠብቃቸዋለህ።
21
በተከበበች ከተማ ውስጥ በነበርኩበት ጊዜ በሚያስደንቅ ሁኔታ ዘላቂ ፍቅሩን የገለጠልኝ እግዚአብሔር ይመስገን!
22
ከድንጋጤዬ የተነሣ ከፊትህ ያራቅኸኝ መስሎኝ ነበር፤ ነገር ግን ርዳታህን ፈልጌ ለምሕረት ወደ አንተ ስጣራ ጩኸቴን ሰማህ።
23
እናንተ ለእርሱ የተቀደሳችሁ ሁሉ እግዚአብሔርን ውደዱት፤ እግዚአብሔር ታማኞችን ይጠብቃል፤ ለትዕቢተኞች ግን ተገቢ ቅጣታቸውን ይሰጣል።
24
እናንተ በእግዚአብሔር ተስፋ የምታደርጉ ሁሉ ጠንክሩ፤ በርቱም።
← Chapter 30
Chapter 32 →