bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Psalms 29
Psalms 29
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
1
እናንተ የሰማይ መላእክት ሁሉ፥ ክብርና ኀይል የእግዚአብሔር ነው በሉ።
2
ክብር ለእግዚአብሔር መሆኑን ግለጡ፤ በቅድስናና በግርማ ሞገስ ለተመላ አምላክ ስገዱ።
3
የእግዚአብሔር ድምፅ በውቅያኖሶች ላይ ያስተጋባል፤ የክብር አምላክ እግዚአብሔር ከሚናወጠው ማዕበል በላይ ያንጐደጒዳል።
4
የእግዚአብሔር ድምፅ ኀያል ነው፤ ድምፁም ባለ ግርማ ነው።
5
የእግዚአብሔር ድምፅ የሊባኖስን ዛፍ ይሰብራል፤ እግዚአብሔር የሊባኖስን ዛፍ ይሰብራል።
6
የሊባኖስን ተራራዎች እንደ እንቦሳ እንዲፈነጩ ያደርጋቸዋል፤ የስርዮንንም ተራራ እንደ ጐሽ ጥጃ እንዲዘል ያደርገዋል።
7
የእግዚአብሔር ድምፅ መብረቅን ብልጭ ያደርጋል።
8
የእግዚአብሔር ድምፅ በረሓን ያናውጣል፤ የቃዴስንም በረሓ ያንቀጠቅጣል፤
9
የእግዚአብሔር ድምፅ አጋዘንን እንድትወልድ ያደርጋል የዛፎችን ቅጠል ያረግፋል፤ በመቅደሱም ያሉ ድምፁን ሲሰሙ “ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን!” ይላሉ።
10
እግዚአብሔር የጥልቁ ባሕር ገዢ ነው፤ በንጉሥነቱም ለዘለዓለም ይገዛል።
11
እግዚአብሔር ለሕዝቡ ኀይልን ይሰጣል፤ በሰላም ይባርካቸዋል።
← Chapter 28
Chapter 30 →