bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Psalms 26
Psalms 26
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
1
እግዚአብሔር ሆይ! በቅንነትና ባለማወላወል በአንተ ተማምኜ ስለ ኖርኩ ፍረድልኝ።
2
እግዚአብሔር ሆይ! ፈትነኝ፤ ምኞቴንና ሐሳቤንም መርምር።
3
የማያቋርጠው ፍቅርህ በዐይኖቼ ፊት ነው፤ ዘወትር የሚመራኝም የአንተ ታማኝነት ነው።
4
ከአታላዮች ጋር አልወዳጅም፤ ከግብዞችም ጋር አልተባበርም፤
5
የክፉ አድራጊዎችን ጉባኤ እጠላለሁ፤ ከክፉዎችም ጋር መቀመጥ አልፈቅድም።
6
እግዚአብሔር ሆይ! ንጹሕነቴን ለማሳየት እጆቼን እታጠባለሁ፤ መሠዊያህንም በመዞር አንተን አመልካለሁ።
7
የምስጋና መዝሙር እየዘመርኩ፥ የአንተን ድንቅ ሥራዎች ሁሉ እናገራለሁ።
8
እግዚአብሔር ሆይ! አንተ የምትኖርበትን ቤትና ክብርህ የሚገኝበትን ስፍራ እወዳለሁ።
9
ደም አፍሳሾች ከሆኑ ኃጢአተኞች ጋር ነፍሴን አትውሰድ፤ ሕይወቴንም አታጥፋ።
10
እነርሱም ጣቶቻቸው ክፉ ሥራን ለመሥራት የነቁ፥ ቀኝ እጆቻቸውም በጉቦ የተሞሉ ናቸው።
11
እኔ በበኩሌ ነቀፋ የሌለበት ሕይወት እኖራለሁ፤ ምሕረትን አድርግልኝ፤ አድነኝም!
12
እግሮቼ በተስተካከለ ምድር ላይ ቆመዋል፤ እግዚአብሔርንም በጉባኤው ሁሉ ፊት አመሰግነዋለሁ።
← Chapter 25
Chapter 27 →