bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Psalms 24
Psalms 24
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
1
ምድርና በምድር ላይ የሚኖሩ ሁሉ፥ የእግዚአብሔር ናቸው፤ ዓለምና በውስጥዋ ያሉት ሁሉ የእርሱ ናቸው።
2
ምድርን በባሕር ላይ የመሠረተው፥ ከውሃ በላይም ያጸናው እርሱ ነው።
3
ወደ እግዚአብሔር ተራራ ማን ይወጣል፤ በተቀደሰ ስፍራውስ ማን ይቆማል።
4
ይህን ማድረግ የሚችል፥ እጆቹ ከክፉ ሥራና ልቡም ከክፉ ሐሳብ ንጹሓን የሆኑ፥ ጣዖትን የማያመልክ፥ ዋሽቶ የማይምል ነው።
5
እንዲህ ዐይነቱ ሰው ከአዳኝ አምላኩ ከእግዚአብሔር በረከትንና ፍትሕን ይቀበላል።
6
ወደ እግዚአብሔር የሚቀርቡና የያዕቆብን አምላክ ፊት የሚሹ እንደዚህ ያሉት ሰዎች ናቸው።
7
እናንተ በሮች ራሳችሁን ከፍ አድርጉ፤ የክብር ንጉሥ ይገባ ዘንድ እናንተ ጥንታውያን በሮች ተከፈቱ።
8
ይህ የክብር ንጉሥ ማነው? እርሱ ብርቱና ኀያሉ እግዚአብሔር ነው። እርሱ በጦርነት ኀያሉ እግዚአብሔር ነው።
9
እናንተ በሮች ራሳችሁን ከፍ አድርጉ የክብር ንጉሥ ይገባ ዘንድ እናንተ ጥንታውያን በሮች ተከፈቱ።
10
ይህ የክብር ንጉሥ ማን ነው? ይህ የክብር ንጉሥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው!
← Chapter 23
Chapter 25 →