bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Psalms 149
Psalms 149
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
1
እግዚአብሔርን አመስግኑ! ለእግዚአብሔር አዲስ መዝሙር ዘምሩ! በምእመናን ጉባኤ አመስግኑት!
2
የእስራኤል ሕዝቦች በፈጣሪያችሁ ደስ ይበላቸው! የጽዮን ሕዝቦችም በንጉሣችሁ ሐሤት ያድርጉ!
3
በማሸብሸብ ስሙን ያመስግኑት፤ ከበሮ እየመቱና በገና እየደረደሩ ያመስግኑት።
4
እግዚአብሔር በሕዝቡ ደስ ይለዋል፤ ድል በማቀዳጀት ትሑታንን ያከብራቸዋል።
5
የእግዚአብሔር ሕዝቦች በድል አድራጊነታቸው ደስ ይበላቸው፤ ሌሊቱን በሙሉ በደስታ ይዘምሩ።
6
ስለ ታም ሰይፍ በእጆቻቸው ይዘው እልል እያሉ እግዚአብሔርን በከፍተኛ ድምፅ ያመስግኑት።
7
እንደዚህ ቢያደርጉ መንግሥታትን ለማሸነፍ፥ አሕዛብንም ለመቅጣት፥
8
ንጉሦቻቸውን በሰንሰለት ለመያዝ፥ መኳንንቶቻቸውን በእግር ብረት ለማሰር፥
9
እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ የደነገገውን በመፈጸም የእግዚአብሔር ሕዝቦች ድልን ይጐናጸፋሉ። እግዚአብሔር ይመስገን።
← Chapter 148
Chapter 150 →