bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Psalms 137
Psalms 137
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
1
በባቢሎን ወንዞች አጠገብ ተቀምጠን፥ ጽዮንን ባስታወስናት ጊዜ አለቀስን።
2
እዚያ በገናዎቻችንን በአኻያ ዛፎች ላይ ሰቀልን።
3
የማረኩንና ሥቃይ የሚያሳዩን ሰዎች በመዘመር እንድናስደስታቸው “ከጽዮን መዝሙሮች አንዱን ለእኛ ዘምሩልን” አሉን።
4
ለእግዚአብሔር መቅረብ የሚገባውን መዝሙር በባዕድ አገር እንዴት እንዘምራለን?
5
ኢየሩሳሌም ሆይ! አንቺን ብረሳሽ በገና የምጫወትበት ቀኝ እጄ ይክዳኝ፤
6
አንቺን ባላስታውስሽና ታላቅ ደስታዬ አድርጌ ባልቈጥርሽ ምላሴ ከትናጋዬ ይጣበቅ።
7
እግዚአብሔር ሆይ! ኢየሩሳሌም በተያዘችበት ቀን ኤዶማውያን ያደረጉትን አስብ፤ “እስከ መሠረትዋ አፈራርሳችሁ ጣሉአት!” እያሉ መጮኻቸውንም አስታውስ።
8
ባቢሎን ሆይ! አፍራሽዋ ባቢሎን! በእኛ ላይ ያደረግሽብንን የክፋት ብድራት ሁሉ በአንቺ ላይ የሚመልስብሽ የተባረከ ነው።
9
ሕፃናት ልጆችሽን እያነሣ በአለት ላይ የሚፈጠፍጣቸው የተባረከ ነው።
← Chapter 136
Chapter 138 →