bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Psalms 132
Psalms 132
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
1
እግዚአብሔር ሆይ! ልቤ በኩራት የተወጠረ አይደለም፤ ዳዊትን አስታውሰው፤ የተቀበለውን መከራ ሁሉ አትርሳ።
2
እግዚአብሔር ሆይ! ለአንተ የገባውን ቃል ኪዳንና ሁሉን ለምትችል ለያዕቆብ አምላክ ለአንተ እንዲህ ሲል የተሳለውን ስእለት አስታውስ፤
3
“ለእግዚአብሔር የመኖሪያ ስፍራ እስከማዘጋጅ፥ ለያዕቆብ አምላክ ቤት እስከምሠራ ድረስ፥ ወደ ቤት አልገባም፤ ወይም በአልጋ ላይ አልተኛም፤ ዕረፍት ወይም እንቅልፍ አይኖረኝም።”
6
በኤፍራታ ሆነን ስለ ቃል ኪዳኑ ታቦት ሰማን፤ በጁአሪም ምድር አገኘነው።
7
ከዚህ በኋላ “ኑ ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ፤ በእግሩ ማረፊያ ሥር እንስገድ” አልን።
8
እግዚአብሔር ሆይ! የኀይልህ መግለጫ ከሆነችው ከቃል ኪዳን ታቦት ጋር ወደምታርፍበት ወደ ቤተ መቅደስ ግባ።
9
ካህናትህ የጽድቅን ሥራ ይሥሩ! ታማኞችህ በደስታ ይዘምሩ!
10
ስለ አገልጋይህ ስለ ዳዊት ስትል መርጠህ የቀባኸውን አትተወው።
11
እግዚአብሔር ለዳዊት እንዲህ ሲል የማይሻር ቃል ኪዳን ገባለት፦ “ከልጆችህ አንዱን አነግሠዋለሁ፤
12
ልጆችህ ቃል ኪዳኔንና የምሰጣቸውን ትእዛዞች ከጠበቁ ልጆቻቸው ከአንተ በኋላ ለዘለዓለም ይነግሣሉ።”
13
እግዚአብሔር ጽዮንን መርጦአታል፤ መኖሪያውም ሊያደርጋት ይፈልጋል።
14
ይህች የዘለዓለም ማረፊያ ስፍራዬ ናት፤ በዚያች ለመኖር እመኝ ስለ ነበር መኖሪያዬ አደረግኋት።
15
ለጽዮን ምግብዋን አበዛለሁ፤ ድኾችዋንም እስከሚጠግቡ አበላቸዋለሁ።
16
ካህናትዋን በሚያደርጉት ሁሉ እባርካቸዋለሁ፤ በውስጥዋም የሚኖሩ ታማኞች በደስታ ይዘምራሉ።
17
ከዳዊት ዘር ንጉሥ እንዲወጣ አደርጋለሁ፤ የቀባሁትንም ኀያል አደርገዋለሁ።
18
ጠላቶቹ ኀፍረትን እንዲከናነቡ አደርጋቸዋለሁ፤ እርሱ ግን የሚያንጸባርቅ ዘውድ ይቀዳጃል።
← Chapter 131
Chapter 133 →