bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Psalms 129
Psalms 129
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
1
ከወጣትነቴ ጀምሮ አደጋ ደርሶብኛል፤ እስራኤላውያን እንዲህ ይበሉ፦
2
“ከወጣትነቴ ጀምሮ ጠላቶቼ በጭካኔ አሳደዱኝ፤ ነገር ግን አላሸነፉኝም።
3
ጀርባዬን በጅራፍ ተልትለው፥ የታረሰ ማሳ አስመስለውታል።
4
እግዚአብሔር ሁልጊዜ ትክክለኛ ነው፤ ከእነዚያ ጨካኞች ገመድ ነጻ አውጥቶኛል።”
5
ጽዮንን የሚጠላ ሁሉ ይሸነፍ! ወደ ኋላውም ይመለስ!
6
በቤት ጣራ ላይ እንደሚበቅልና ከማደጉ በፊት እንደሚደርቅ ሣር ይሁን።
7
እንዲህ ዐይነቱን ሣር ማንም አይሰበስበውም፤ ወይም ነዶው በእጁ አይሞላም።
8
በአጠገባቸው የሚያልፉት ሁሉ ለጽዮን ጠላቶች “እግዚአብሔር ይባርካችሁ! እኛም በእግዚአብሔር ስም እንባርካችኋለን!” አይሉአቸውም።
← Chapter 128
Chapter 130 →