bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Psalms 126
Psalms 126
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
1
እግዚአብሔር ወደ ኢየሩሳሌም መልሶ ባመጣን ጊዜ ሕልም እንጂ እውነት አልመሰለንም ነበር።
2
አፋችን በሳቅ ተሞላ፤ አንደበታችንም የደስታ መዝሙር ዘመረ፤ በዚህም ምክንያት አሕዛብ፦ “እግዚአብሔር ታላቅ ነገር አደረገላቸው” አሉን።
3
በእርግጥም ብዙ ታላላቅ ነገሮችን አድርጎልናል፤ እጅግም ተደስተናል።
4
እግዚአብሔር ሆይ! ዝናብ ለደቡብ በረሓ ወንዝ ውሃን እንደሚሰጥ የተማረከብን ሀብታችንን መልስልን።
5
በእንባ የሚዘሩ የደስታ መዝሙር እየዘመሩ ይሰበሰባሉ።
6
ዘሩን ተሸክመው ሲሄዱ ያለቅሱ የነበሩት፥ በደስታ እየዘመሩ ነዶአቸውን ተሸክመው ይመለሳሉ።
← Chapter 125
Chapter 127 →