bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Psalms 124
Psalms 124
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
1
እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ባይሆን ምን ይበጀን ነበር? እስራኤል እንዲህ ብሎ ይመልስ፤
2
“እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ባይሆን ጠላቶቻችን ባጠቁን ጊዜ
3
በታላቅ ቊጣ በእኛ ላይ ተነሥተው ከነሕይወታችን በዋጡን ነበር፤
4
ጐርፍ በወሰደን፥ ውሃም በሸፈነን ነበር፤
5
ብርቱ ማዕበልም ባሰጠመን ነበር።”
6
ጠላቶቻችን እንዲደመስሱን ያላደረገ እግዚአብሔር ይመስገን።
7
እንደ ወፍ ከአዳኞች ወጥመድ አምልጠናል፤ ወጥመዱ ተሰበረ፤ እኛም ነጻ ወጣን።
8
ይህንንም ርዳታ ያገኘነው ሰማይንና ምድርን ከፈጠረ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።
← Chapter 123
Chapter 125 →