bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Psalms 122
Psalms 122
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
1
“ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ!” ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ።
2
ኢየሩሳሌም ሆይ! በበሮችሽ ገብተን በውስጥ ቆመናል።
3
ኢየሩሳሌም እርስ በርስዋ ተጠጋግታና ተጠናክራ የተሠራች ከተማ ናት።
4
በትእዛዙ መሠረት ለእግዚአብሔር ምስጋና ለማቅረብ የእስራኤል ነገዶች ሁሉ የሚሰበሰቡት ወደዚህች ከተማ ነው።
5
ከዳዊት ዘር የነገሡ ሁሉ ሕዝባቸውን ለመዳኘት በዚህች ከተማ ይቀመጡ ነበር።
6
በኢየሩሳሌም ከተማ ሰላም እንዲሆን እንዲህ ብላችሁ ጸልዩ፤ “የሚወዱሽ ሁሉ ይበልጽጉ፤
7
በቅጥሮችሽ ውስጥ ሰላም ይሁን፤ በቤተ መንግሥትሽም ውስጥ ጸጥታ ይኑር።”
8
በዘመዶቼና በወዳጆቼ ምክንያት ኢየሩሳሌምን “ሰላም ከአንቺ ጋር ይሁን!” እላታለሁ።
9
ኢየሩሳሌም ሆይ! በአምላካችን በእግዚአብሔር ቤት ምክንያት ለአንቺ መልካም ነገር እንዲሆንልሽ እመኛለሁ።
← Chapter 121
Chapter 123 →