bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Psalms 116
Psalms 116
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
1
ጩኸቴንና ልመናዬን ስለ ሰማ እግዚአብሔርን እወደዋለሁ።
2
እርሱን በምጠራው ጊዜ ሁሉ ስለሚሰማኝ፥ በዘመኔ ሁሉ ወደ እርሱ እጮኻለሁ።
3
የሞት አደጋ ዙሪያዬን ከበበኝ፤ የመቃብር አስፈሪ ሁኔታ አሠቀቀኝ፤ በችግርና በሐዘን ተሸነፍኩ።
4
በዚያን ጊዜ “አምላክ ሆይ! እባክህ አድነኝ!” ብዬ ወደ እግዚአብሔር ጮኽኩ።
5
እግዚአብሔር ቸርና እውነተኛ ነው፤ አምላካችን መሐሪ ነው።
6
እግዚአብሔር የዋሆች የሆኑትን ይጠብቃል፤ እኔ በተቸገርኩ ጊዜ አድኖኛል።
7
እግዚአብሔር መልካም ነገር ስላደረገልኝ፥ ከእንግዲህ ወዲያ አልጨነቅም።
8
እግዚአብሔር ከሞት አዳነኝ፤ እንባዬ እንዲቆም አደረገ፤ እግሮቼንም ከመደናቀፍ ጠበቃቸው።
9
ስለዚህ ሕያዋን በሚገኙበት በእግዚአብሔር ፊት እኖራለሁ።
10
“እጅግ ተሠቃየሁ” ባልኩበት ጊዜ እንኳ አንተን ማመኔን አልተውኩም።
11
በፍርሃቴ ጊዜ እንኳ “ማንም የሚታመን የለም” አልኩ።
12
ስላደረገልኝ መልካም ነገር ሁሉ ለእግዚአብሔር ምን ውለታ ልመልስ እችላለሁ?
13
እግዚአብሔር ስላዳነኝ አመሰግነዋለሁ፤ የወይን ጠጅ መባም አቀርብለታለሁ።
14
በሕዝብ ጉባኤ ፊት ተገኝቼ ለእግዚአብሔር የተሳልኩትን አቀርባለሁ።
15
የቅዱሳን ሞት በእግዚአብሔር ዘንድ የከበረ ነው።
16
እግዚአብሔር ሆይ! እኔ የአንተ ነኝ፤ የብላቴናይቱ አገልጋይህ ልጅ ነኝ፤ እስራቴን ፈተህልኛል። ከሞት ያዳንከኝ አንተ ነህ።
17
የምስጋና መሥዋዕት አቀርብልሃለሁ፤ ወደ አንተም እጸልያለሁ።
18
በእርሱ ሕዝብ ጉባኤ ፊት ተገኝቼ ለእግዚአብሔር የተሳልኩትን አቀርባለሁ፤
19
የማቀርበውም በኢየሩሳሌም መካከል በሚገኘው በእግዚአብሔር ቤት አደባባይ ነው። እግዚአብሔር ይመስገን!
← Chapter 115
Chapter 117 →