bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Psalms 103
Psalms 103
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
1
ነፍሴ ሆይ! እግዚአብሔርን አመስግኚ! የእግዚአብሔርን ቅዱስ ስም በሙሉ ልቤ አመሰግናለሁ።
2
ነፍሴ ሆይ! እግዚአብሔርን አመስግኚ! ቸርነቱንም አትርሺ!
3
ኃጢአቴን ሁሉ ይቅር ይላል፤ ሕመሜንም ሁሉ ይፈውሳል።
4
ወደ መቃብር ከመውረድ ይጠብቀኛል፤ በፍቅርና በምሕረትም ይባርከኛል።
5
በጐልማሳነቴ ሕይወቴን በመልካም ነገር ሁሉ ይሞላታል፤ እንደ ንስርም ወጣትነቴን ያድሳል።
6
እግዚአብሔር በሚሠራው ሁሉ ጻድቅ ነው፤ ለተጨቈኑት ፍትሕን ይሰጣል።
7
ዕቅዱን ለሙሴ ገለጠለት፤ የእስራኤል ሕዝቦች አስደናቂ ሥራዎቹን እንዲያዩ አደረገ።
8
እግዚአብሔር መሐሪና ይቅር ባይ ነው። በቶሎ የማይቈጣና ለዘለዓለም ታማኝ ነው።
9
ዘወትር የሚገሥጽ አይደለም፤ ቊጣውም ለዘለዓለም አይቈይም።
10
በኃጢአታችን መጠን አልቀጣንም፤ በበደላችንም ልክ አልከፈለንም።
11
ሰማይ ከምድር ከፍ የሚለውን ያኽል እግዚአብሔር ለሚፈሩት የሚሰጠው ፍቅር ታላቅ ነው።
12
ምሥራቅ ከምዕራብ የሚርቀውን ያኽል እግዚአብሔር ኃጢአታችንን ከእኛ ያርቀዋል።
13
አባት ለልጆቹ የሚራራላቸውን ያኽል እግዚአብሔርም የሚፈሩትን ይራራላቸዋል።
14
እግዚአብሔር ከምን እንደ ተፈጠርን ያውቃል፤ ዐፈር መሆናችንንም ያስታውሳል።
15
የሰው ሕይወት እንደ ሣር ነው፤ እንደሚያድግና እንደሚያብብ እንደ ዱር አበባ ነው።
16
የዱር አበባ ነፋስ በሚነፍስበት ጊዜ ወዲያው ይጠፋል፤ በዚያ ስፍራ እንደ ነበረ እንኳ አይታወቅም።
17
ነገር ግን እግዚአብሔር ለሚያከብሩት ሁሉ ፍቅሩን ለዘለዓለም ያሳያቸዋል፤ ቸርነቱም ከትውልድ ወደ ትውልድ ይተላለፋል።
18
ይህንንም የሚያደርገው ቃል ኪዳኑን ቢጠብቁ፥ ትእዛዙንም በታማኝነት ቢፈጽሙ ነው።
19
የእግዚአብሔር ዙፋን በሰማይ ነው፤ የእርሱም ገዢነት በሁሉም ላይ ነው።
20
ትእዛዞቹን የምትፈጽሙ የሚናገረውን የምታዳምጡ፤ እናንተ ኀያላንና ብርቱዎች መላእክቱ እግዚአብሔርን አመስግኑ።
21
አገልጋዮቹ የሆናችሁ፥ ፈቃዱንም የምትፈጽሙ፥ እናንተ የሰማይ ሠራዊት እግዚአብሔርን አመስግኑ!
22
በግዛቱ ሁሉ የምትገኙ ፍጥረቶቹ እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ነፍሴ ሆይ! እግዚአብሔርን አመስግኚ!
← Chapter 102
Chapter 104 →