bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Job 40
Job 40
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
1
ቀጥሎም እግዚአብሔር ኢዮብን እንዲህ አለው፦
2
“ኢዮብ ሆይ! ለመሆኑ ሰው ሁሉን ከሚችል አምላክ ከእኔ ጋር ተከራክሮ ሊረታ የሚችል ይመስልሃልን? ከእኔ ከእግዚአብሔር ጋር የምትከራከር አንተ ስለ ሆንክ፥ እስቲ መልስ ስጥ።”
3
ኢዮብም እንዲህ ሲል መለሰ፦
4
“ጌታ ሆይ! እኔ ለምንም የማልጠቅም ከንቱ ሰው ነኝ፤ ከእንግዲህ ወዲህ አፌን በእጄ ይዤ ዝም ከማለት በስተቀር፥ ለአንተ የምሰጠው መልስ የለኝም።
5
አንድ ጊዜ፥ ወይም ሁለት ጊዜ ተናገርኩ፤ ከእንግዲህ ወዲያ ከቶ አልናገርም። እግዚአብሔር
6
ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር በዐውሎ ነፋስ ውስጥ ሆኖ ኢዮብን እንዲህ አለው፦
7
“ተነሥና እንደ ወንድ ወገብህን ታጠቅ፤ እጠይቅሃለሁ፤ አንተም መልስልኝ።
8
እኔን ፍርደ ገምድል አድርገህ በመክሰስ ራስህን ንጹሕ ለማድረግ ትሞክራለህን?
9
ለመሆኑ ኀይልህ እንደ እኔ እንደ እግዚአብሔር ኀይል የበረታ ነውን? ድምፅህስ እንደ እኔ እንደ እግዚአብሔር ድምፅ ኀያል ነውን?
10
ይህ ከሆነ ራስህን በግርማ ሞገስ ተቀዳጅ ክብርንና ገናናነትንም ተጐናጸፍ።
11
ትዕቢተኞችን ተመልክተህ አዋርዳቸው፤ ቊጣህንም በላያቸው አፍስስ።
12
በጥንቃቄ ሁሉን ተመልክተህ አሳፍራቸው፤ ክፉዎችንም ባሉበት ስፍራ አጥፋቸው።
13
በከፈን ጨርቅም ጠቅልለህ ሁሉንም በአንድነት በመሬት ውስጥ ቅበራቸው።
14
ከዚያ በኋላ እኔም በተራዬ በራስህ ኀይል ድልን እንደምትቀዳጅ እመሰክርልሃለሁ።
15
“እኔ አንተንና ጒማሬን ፈጥሬአለሁ፤ ጉማሬውም እንደ በሬ ሣር ይበላል።
16
በወገቡ ላይ ያለውን ጥንካሬና በሆዱ ውስጥ ያለውን የጅማት ብርታት ተመልከት።
17
ጅራቱ እንደ ሊባኖስ ዛፍ ቀጥ ያለ ነው፤ የጭኑም ጅማት ወፍራምና ጠንካራ ነው።
18
አጥንቶቹ እንደ ነሐስ ናቸው። እንደ ብረት ዘንጎችም የጠነከሩ ናቸው።
19
“እኔ ከፈጠርኳቸው ፍጥረቶች ሁሉ ኀያል ከእኔ በቀር የሚያሸንፈው የለም።
20
የዱር እንስሶች የሚፈነጩበት ተራራ ለእርሱ ምግብን ያበቅልለታል።
21
ጥላ ካለው ዛፍና በደንገል መካከል በረግረግ ውስጥ ይተኛል።
22
ጥላ ያላቸው ዛፎች በጥላው ይሰውሩታል። የአኻያ ዛፎችም ይከቡታል።
23
በወንዝ ውሃ ሙላት ከቶ አይደነግጥም፤ የዮርዳኖስ ወንዝ እንኳ እስከ አፉ ቢጐርፍበት አይሰጋም፥
24
ዐይኑን በማጥፋትና አፍንጫውን በመሰነግ፥ ጒማሬን ሊይዘው የሚችል ማነው?
← Chapter 39
Chapter 41 →