bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Job 35
Job 35
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
1
ኤሊሁም ንግግሩን በመቀጠል እንዲህ አለ፦
2
“ኢዮብ ሆይ! በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ ነኝ ማለትህ ትክክል ነውን?
3
‘ኃጢአት ባልሠራ ምን እጠቀማለሁ? ምንስ አተርፋለሁ?’ ብለህ ትጠይቅ ይሆናል።
4
አሁን እኔ ለአንተና ከአንተ ጋር ላሉ ለባልንጀሮችህ፥ መልስ እሰጣለሁ።
5
“ቀና ብለህ ወደ ሰማይ ተመልከት፤ ከአንተ በላይ ከፍ ብሎ የሚታየውንም ደመና አስተውል።
6
ኃጢአትን ብትሠራ እግዚአብሔርን በምን ትጐዳዋለህ? በደልስ ብታበዛ ምን ታደርገዋለህ?
7
ጻድቅ ብትሆን ለእግዚአብሔር ምን ትሰጠዋለህ? እርሱ ከአንተ ምንም አይፈልግም።
8
ኃጢአት ብትሠራ የምትጐዳው እንደ አንተ ያለውን ሰው ነው፤ መልካም ሥራ ብትሠራ፥ የምትጠቅመው ሰውን ነው።
9
ሰዎች ጭቈና ሲበዛባቸው ይጮኻሉ፤ ከሚበረታባቸውም እጅ የሚታደጋቸውን ለማግኘት፥ አቤቱታ ያሰማሉ።
10
ነገር ግን ከእነርሱ አንዳቸው እንኳ በሌሊት ጥበቃ የሚያደርገው ፈጣሪ አምላክ ወዴት ነው ብሎ አይጠይቅም።
11
ከእንስሶች አብልጦ ያስተማረን ከወፎችም ይልቅ ጥበበኞች ያደረገን እርሱ ነው።
12
እነርሱ ይጮኻሉ እርሱ ግን ትዕቢተኞችና ክፉዎች ስለ ሆኑ መልስ አይሰጣቸውም።
13
በእርግጥ እግዚአብሔር ከልብ ያልሆነ ጩኸትን አይሰማም፤ ሁሉን የሚችል አምላክም አያተኲርበትም።
14
“ምንም እንኳ እግዚአብሔርን አላየውም ብትል ጉዳይህ በእርሱ ፊት ስለ ሆነ በትዕግሥት ልትጠብቀው ይገባል።
15
እንዲሁም እግዚአብሔር በቊጣው የማይቀጣ፥ የሰውንም ክፋት በቸልታ የሚያልፍ ይመስልሃል?
16
ኢዮብ ሆይ! በከንቱ ንግግር ታበዛለህ፤ ያለ ዕውቀትም ባዶ ቃላትን ትለፈልፋለህ።”
← Chapter 34
Chapter 36 →