bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Job 27
Job 27
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
1
ኢዮብም ንግግሩን በመቀጠል እንዲህ አለ፦
2
“ትክክለኛ ፍርድ በመከልከል፥ ሕይወቴን እጅግ መራራ ባደረገው ሁሉን በሚችል በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ።
3
እግዚአብሔር የሕይወት እስትንፋስ ሰጥቶኝ እስከ አለሁ ድረስ
4
ከቶ ክፉ ቃል ከአፌ አይወጣም፤ በአንደበቴም ሐሰት አልናገርም።
5
እናንተ የተናገራችሁት ሁሉ ትክክል ነው ብዬ በፍጹም አልቀበልም፤ እስከምሞትበት ቀን ድረስ በቅንነት መጽናቴን አልተውም።
6
“በእውነተኛነቴ እጸናለሁ፤ እርሱንም አልተውም፤ በሕይወት በምኖርበት ዘመን ሁሉ ኅሊናዬ በዚህ ነገር አይወቅሰኝም።
7
“ጠላቶቼ እንደ ኃጢአተኞች፥ ተቃዋሚዎቼም እንደ ግፈኞች ይፈረድባቸው።
8
እግዚአብሔር ነፍሳቸውን ከሥጋቸው በመለየት ዕድሜአቸውን ባሳጠረ ጊዜ፥ እግዚአብሔርን የሚክዱ ሰዎች ምን ተስፋ ይኖራቸዋል?
9
መከራ በሚመጣባቸው ጊዜ እግዚአብሔር ጩኸታቸውን ይሰማልን?
10
ሁሉን በሚችል አምላክ ይደሰታሉን? በየጊዜውስ የእግዚአብሔርን ስም ይጠራሉን?
11
“የእግዚአብሔር ኀይል ምን ያኽል ታላቅ እንደ ሆነ አስተምራችኋለሁ፤ ሁሉን የሚችል አምላክ ያቀደውንም አልሸሽግባችሁም፤
12
እናንተም እኮ ይህን ሁሉ ታውቃላችሁ፤ ታዲያ ይህን ከንቱ ነገር ለምን ትናገራላችሁ?”
13
“እነሆ ሁሉን የሚችል አምላክ ክፉ ሰውንና ግፈኛን የሚቀጣው በዚህ ዐይነት ነው፤
14
ልጆቹ ቢበዙ በጦርነት ያልቃሉ፤ ዘሮቹም ምግብ አጥተው ይራባሉ።
15
ከዚህ የተረፉትም በበሽታ ያልቃሉ፤ መበለቶቻቸው እንኳ አያለቅሱላቸውም።
16
ክፉ ሰው ብርን እንደ ዐፈር ሊያጋብስ፥ ልብስንም እንደ ሸክላ ሊከምር ይችላል፤
17
ዳሩ ግን ክፉ ሰው የሰበሰበውን ልብስ ጻድቅ ይለብሰዋል፤ ያካበተውንም ብር ንጹሖች ይካፈሉታል።
18
የሚሠራው ቤት እንደ ሸረሪት ድርና እንደ ሰብል ጠባቂ ጎጆ ይፈራርሳል።
19
ክፉ ሰው ለመጨረሻ ጊዜ ሀብታም ሆኖ ይተኛል፤ ሲነቃ ግን ሀብቱ ሁሉ ጠፍቶአል።
20
ድንጋጤ እንደ ጐርፍ በድንገት ይደርስበታል፤ በሌሊትም ዐውሎ ነፋስ ይነጥቀዋል።
21
የምሥራቅ ነፋስ ከመኖሪያ ቤቱ ጠራርጎ ይወስደዋል፤
22
ሸሽቶ ለማምለጥ ቢሞክርም ነፋሱ ያለ ርኅራኄ በእርሱ ላይ ያይልበታል፤
23
ነፋሱ በእርሱ ላይ አጨበጨበ፤ በአለበትም ቦታ ሆኖ አፏጨበት።
← Chapter 26
Chapter 28 →