bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Job 23
Job 23
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
1
ኢዮብም እንዲህ ሲል መለሰ፦
2
“አሁንም ልቤ በመረረ ሐዘንና ሮሮ የተሞላ ነው፤ በመቃተት ብጮኽም እጁ በእኔ ላይ እንደ ከበደች ናት።
3
የሚገኝበትን ቦታ ባውቅ እንዴት በወደድሁ ነበር፤ ወደሚኖርበትም ቦታ ብደርስ እንዴት ደስ ባለኝ ነበር፤
4
አቤቱታዬን በፊቱ አሰማ ነበር፤ የመከላከያ መልሴንም በዝርዝር አቀርብ ነበር።
5
የሚሰጠኝን መልስ ዐውቅ ነበር፤ ምን እንደሚለኝም እረዳ ነበር።
6
ታዲያ፥ እግዚአብሔር በታላቅ ኀይሉ ይፋረደኝ ይሆን? አይደለም፤ ነገር ግን ነገሬን ያዳምጣል።
7
በዚያ ቅን ሰው ከእርሱ ጋር ይከራከራል፤ ዳኛዬ እግዚአብሔርም ለዘለዓለም ነጻ ያወጣኛል።
8
“ነገር ግን ወደ ምሥራቅ ብሄድ በዚያ የለም፤ ወደ ምዕራብም ብመለስ ላገኘው አልቻልኩም።
9
እርሱ በሰሜን ሥራውን ይሠራል፤ እኔ ግን ላየው አልቻልኩም፤ ወደ ደቡብም ብዞር ላገኘው አልቻልኩም።
10
እርሱ እርምጃዬን ሁሉ ያውቃል፤ ቢፈትነኝም እንደ ወርቅ ንጹሕ ሆኜ ያገኘኛል።
11
እግሮቼ እርሱ በሚወደው መንገድ ይሄዳሉ፤ በማወላወል ወደ ግራም ወደ ቀኝም አልልም።
12
ከእርሱ ትእዛዞች አልወጣሁም፤ ቃሉንም በልቤ ውስጥ ጠብቄአለሁ።
13
“እርሱ ራሱ ይወስናል፤ እርሱንም የሚቃወም የለም፤ እርሱ የወደደውን ሁሉ ያደርጋል።
14
በእኔ ላይ ያቀደውን ሁሉ ይፈጽመዋል፤ ይህንንም የሚመስሉ ብዙ ዕቅዶች አሉት።
15
ስለዚህ በእርሱ ፊት መቆም እጅግ ያስፈራኛል፤ ይህን ባሰብኩ ጊዜ እንኳ ፈራሁ።
16
እግዚአብሔር ልቤ እንዲዝል አደረገው፤ ሁሉን የሚችል አምላክ አስደነገጠኝ።
17
ምንም እንኳ ድቅድቅ ጨለማ ዐይኔን ቢጋርደኝ፥ የጨለማው ክብደት ከመናገር እንድቈጠብ አላደረገኝም።”
← Chapter 22
Chapter 24 →