bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Jeremiah 47
Jeremiah 47
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
1
የግብጽ ንጉሥ በጋዛ ላይ አደጋ ከመጣሉ በፊት እግዚአብሔር ስለ ፍልስጥኤም እንዲህ ሲል ተናገረኝ፦
2
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፥ ውሃ ከሰሜን በኩል ተነሥቶ በጐርፍ እንደ ተሞላ ወንዝ ይፈስሳል፤ ምድርንና በምድር ላይ ያለውን ሁሉ ከተሞችንና በውስጣቸው የሚኖሩትን ሕዝብ በሙሉ ይሸፍናል። ሕዝቡ ሁሉ ርዳታ ለማግኘት ይጮኻሉ፤ በምድር ላይ የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ምርር ብለው ያለቅሳሉ።
3
ከሚጋልቡ ፈረሶች ኮቴ ድምፅ፥ ከጠላት መንኰራኲር ድምፅ፥ ከሠረገሎቻቸው መትመም የተነሣ አባቶች ኀይላቸው በመድከሙ ምክንያት ልጆቻቸውን እንኳ ለመርዳት ወደ ኋላ አይመለሱም።
4
ፍልስጥኤም የምትጠፋበት ጊዜ ደርሶአል፤ ከሞት ተርፈው ጢሮስንና ሲዶናን የሚረዱት ሁሉ ተቈራርጠው የሚቀሩበት ጊዜ ተቃርቦአል። እኔ እግዚአብሔር፥ ከሞት ተርፈው በባሕር ዳርቻ የምትገኘው የካፍቶር ዘሮች የሆኑትን ፍልስጥኤማውያን በሙሉ እደመስሳለሁ።
5
የጋዛ ሕዝብ በሐዘን ጠጒራቸውን ይላጫሉ፤ የአስቀሎና ሕዝብ ሁሉ ጸጥ እንዲሉ ይደረጋሉ። በፍልስጥኤም ሸለቆ ከጥፋት የተረፉትስ ሰውነታቸውን እየቈራረጡ የሚያዝኑት እስከ መቼ ነው?
6
‘የእግዚአብሔር ሰይፍ ሆይ! ከሥራህ የምታርፈው መቼ ነው? እባክህ ወደ አፎትህ ተመልሰህ ዕረፍት አድርግ’ እያላችሁ ትጮኻላችሁ።
7
ነገር ግን እኔ እግዚአብሔር የሰጠሁትን ሥራ ሳይፈጽም እንዴት ማረፍ ይችላል? እኔ በአስቀሎናና በጠረፎችዋ በሚኖሩ ሕዝብ ላይ አደጋ እንዲጥል አዝዤዋለሁ።”
← Chapter 46
Chapter 48 →