bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Isaiah 64
Isaiah 64
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
1
ምነው ሰማያትን ከፍተህ ብትወርድ፤ ተራራዎችም አንተን አይተው ምነው በተንቀጠቀጡ፤
2
እሳት ደረቁን እንጨት በሚያጋይ ጊዜ ፍሙ የተጣደውን ውሃ እንደሚያፍለቀልቀው፥ ሕዝቦችም በአንተ መገለጥ እንዲንቀጠቀጡ ወርደህ ስምህ በጠላቶችህ ዘንድ እንዲታወቅ አድርግ!
3
ከዚህ በፊትም መጥተህ እኛ ያልጠበቅናቸውን እጅግ አስፈሪ የሆኑ ነገሮችን በፈጸምክበት ጊዜ ተራራዎች አንተን አይተው በፍርሃት ተንቀጠቀጡ።
4
ከጥንት ጀምሮ ተስፋቸውን በእርሱ አድርገው ለሚተማመኑበት ወገኖች እነዚያን ሁሉ ድንቅ ነገሮች ያደረገ አምላክ ከአንተ በቀር አልተሰማም፤ አልታየም፤ የተረዳም የለም።
5
የአንተን መንገድ አስታውሰው ፈቃድህን በደስታ የሚፈጽሙትን ትረዳቸዋለህ፤ ፈቃድህን መተላለፍን በቀጠልን ጊዜ ግን አንተ ተቈጣኸን፤ ታዲያ እንዴት ልንድን እንችላለን?
6
እኛ ሁላችን በኃጢአት ረክሰናል፤ ጽድቃችንም እንደ አደፍ ጨርቅ ሆኖአል፤ ከኃጢአታችን ብዛት የተነሣ ደርቀው በነፋስ እንደሚረግፉ ቅጠሎች ሆነናል።
7
በኃጢአታችን ምክንያት ፊትህን ስላዞርክብንና ለበደላችንም ተገዢዎች እንድንሆን ስለ ተውከን ስምህን የሚጠራና አንተን ለማግኘት የሚጥር ማንም የለም።
8
ሆኖም አምላክ ሆይ! አንተ አባታችን ነህ፤ እኛ ሸክላዎች ስንሆን አንተ ሠሪአችን ነህ፤ ሁላችንም የእጅህ ሥራ ነን።
9
አምላክ ሆይ! አምርረህ አትቈጣ፤ ኃጢአታችንንም ለዘለዓለም አታስብብን፤ እኛ ሁላችን ሕዝብህ መሆናችንን አስታውስ።
10
የተቀደሱ ከተሞችህ በረሓ ሆነዋል፤ ጽዮን በረሓ ኢየሩሳሌምም ባድማ ሆነዋል።
11
የቀድሞ አባቶቻችን አንተን ሲያመሰግኑበት የነበረ፥ ቅዱስና ውብ የሆነው ቤተ መቅደስህ በእሳት ጋይቶአል፤ የሚያስደስቱ ነገሮች ሁሉ ፈራርሰዋል።
12
አምላክ ሆይ! ከዚህ ሁሉ በኋላ አንዳች ነገር አታደርግምን? ዝም ብለህስ በኀይለኛ ቅጣት ትቀጣናለህን?
← Chapter 63
Chapter 65 →