bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Isaiah 52
Isaiah 52
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
1
ጽዮን ሆይ! ተነሺ፤ ንቂ! ኀይልሽን እንደ ልብስ ልበሺ! ቅድስቲቱ ከተማ ኢየሩሳሌም ሆይ! የተዋበ ልብስሽን ልበሺ፤ ከእንግዲህ ወዲህ ያልተገረዙና በሥርዓት ያልነጹ ሰዎች ወደ ቅጥርሽ ውስጥ አይገቡም።
2
ምርኮኛይቱ ኢየሩሳሌም ሆይ! ተነሥተሽ ትቢያሽን አራግፊ፤ በዙፋን ላይም ተቀመጪ፤ እናንተም የጽዮን ምርኮኞች ሆይ! የታሰራችሁበትን ሰንሰለት ከአንገታችሁ ፍቱ።
3
እግዚአብሔር ሕዝቡን እንዲህ ይላል፦ “ለባርነት ያለ ዋጋ ተሸጣችሁ ነበር፤ የምትዋጁትም ዋጋ ሳይከፈል ነው።
4
ከዚህ በፊት ወደ ግብጽ ወርዳችሁ በስደት የኖራችሁት በፈቃዳችሁ ነበር፤ አሦራውያን ግን ምንም ሳይከፍሉባችሁ ማርከው በመውሰድ በብርቱ ጨቊነው ገዙአችሁ”።
5
“ሕዝቤ ያለ ዋጋ ሲወሰድ እያየሁ አሁን እኔ የማደርገው ምን አለ? ገዢዎቻቸውም ይሳለቁባቸዋል፤ ያለማቋረጥም ስሜን ይሰድባሉ።
6
ስለዚህ በዚያን ጊዜ ሕዝቤ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን፥ ይህንንም የምናገረው እኔ መሆኔን ያውቃሉ።”
7
በተራሮች ላይ ስለ ሰላምና ስለ መዳን የሚናገር፥ መልካም ዜናንም የሚያበሥር፥ “አምላክሽ ይነግሣል!” ብሎ ለጽዮን የሚነግራት የመልክተኛ እግሩ ምንኛ ድንቅ ነው!
8
እግዚአብሔር ወደ ጽዮን ሲመለስ በግልጽ ስለሚያዩ ከተማ ጠባቂዎችሽ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው የደስታ መዝሙር ሲዘምሩ አድምጪ።
9
እግዚአብሔር ሕዝቡን ያጽናናል ኢየሩሳሌምንም ይታደጋል ስለዚህ እናንተ የኢየሩሳሌም ፍርስራሾች ሆይ! ተባብራችሁ በደስታ ዘምሩ።
10
እግዚአብሔር በሕዝቦች ሁሉ ፊት ኀያልነቱን ይገልጣል፤ መላው ዓለምም የእርሱን አዳኝነት ያያል።
11
እናንተ የቤተ መቅደስን ንዋያተ ቅድሳት የተሸከማችሁ! ከባቢሎን ውጡ፤ ከእርሱም ተለዩ፤ ርኩስ የሆነውን ነገር አትንኩ፤ ከመካከልዋም ወጥታችሁ ራሳችሁን አንጹ።
12
እግዚአብሔር በፊታችሁ ሆኖ ስለሚመራችሁ፥ የእስራኤል አምላክ ከበኋላ ሆኖ ስለሚጠብቃችሁ ስትወጡም በችኰላና በመኰብለል አይሆንም።
13
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፥ አገልጋዬ ሥራው ሁሉ ይከናወንለታል፤ በክብርም እጅግ ከፍ ከፍ ይላል።
14
ከማንኛውም ሰው በላይ መልኩ በጣም ተጐሳቊሎ ስለ ነበረ ሁናቴውን ያዩ ሰዎች አብዛኞቹ በጣም ደነገጡ።
15
ቀድሞ ያልተነገራቸውን ነገር ስለሚያዩና ያልሰሙትን ነገር ስለሚያስተውሉ ብዙ ሕዝቦች ስለ አገልጋዬ ይደነቃሉ፤ ነገሥታትም በእርሱ በመደነቅ የሚናገሩትን ያጣሉ።”
← Chapter 51
Chapter 53 →