bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Isaiah 35
Isaiah 35
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
1
በረሓውና ደረቁ ምድር ደስ ይለዋል፤ በምድረ በዳም አበቦች ያብባሉ።
2
ምድረ በዳዎች በፈኩ አበቦች ይሞላሉ፤ የደስታ መዝሙርም ይዘምራሉ፤ እንደ ሊባኖስ ተራራ ግርማ ያላቸው ይሆናሉ፤ እንደ ቀርሜሎስም ተራራ ወይም እንደ ሻሮን ሸለቆ ክብርን የተጐናጸፉ ይሆናሉ። ሁሉም የእግዚአብሔርን ክብር የአምላካችንንም ግርማ ያያሉ።
3
የደከሙትን ክንዶች አጠንክሩ፥ የተብረከረኩ ጒልበቶችንም አጽኑ።
4
ፈሪ ልብ ላላቸው “እነሆ አምላካችሁ ጠላቶቻችሁን ለመበቀልና የበደላቸውንም ዋጋ ለመክፈል መጥቶ ስለሚያድናችሁ በርቱ! አትፍሩ!” በሉአቸው።
5
በዚያን ጊዜ ዕውሮች ያያሉ፤ ደንቆሮዎች ይሰማሉ፤
6
አንካሶች እንደ ሚዳቋ ይዘላሉ፤ መናገር የማይችሉ ድዳዎች ይዘምራሉ፤ በበረሓ ውስጥ የጅረት ውሃ ይፈስሳል።
7
የሚያቃጥለው አሸዋ ኩሬ ይሆናል፤ ደረቁም ምድር በምንጭ ውሃ ይረሰርሳል፤ የቀበሮዎች መፈንጫ የነበረው ስፍራ ለምለም ሣርና ቄጠማ የሚበቅልበት ይሆናል።
8
በዚያ “ቅዱስ ጐዳና” የሚባል መንገድ ይኖራል፤ እርሱም ለእግዚአብሔር ሰዎች ይሆናል፤ ንጹሕ ያልሆነ ሰው በዚያ መንገድ አይሄድም፤ ሞኞችም ሊሄዱበት አይችሉም።
9
አንበሶችም ሆነ ነጣቂ አውሬዎች በዚያ አይገኙም፤ በዚያ መንገድ የሚመላለሱ እግዚአብሔር የታደጋቸው ወገኖች ብቻ ይሆናሉ።
10
እግዚአብሔር የታደጋቸው ሰዎች ተመልሰው ይመጣሉ፤ እየዘመሩም ወደ ጽዮን ይገባሉ፤ ዘወትር የደስታን ዘውድ ይቀዳጃሉ፤ ተድላና ደስታንም ያገኛሉ፤ ማዘንና መቃተት ከእነርሱ ይርቃል።
← Chapter 34
Chapter 36 →