bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Isaiah 20
Isaiah 20
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
1
የአሦር ንጉሠ ነገሥት በሆነው በሣርጎን ትእዛዝ የአሦራውያን ጦር አዛዥ የፍልስጥኤማውያን ከተማ በሆነችው በአሽዶድ ላይ አደጋ ጣለ፤
2
በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር የአሞጽን ልጅ ኢሳይያስን “ጫማህንና የማቅ ልብስህን አውልቀህ በባዶ እግርህ ሂድ” ብሎ አዘዘው። ኢሳይያስም ለቃሉ በመታዘዝ ዕራቊቱን በባዶ እግሩ ይመላለስ ነበር።
3
እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “አገልጋዬ ኢሳይያስ ዕራቊቱን በባዶ እግሩ ሦስት ዓመት ሙሉ ሲመላለስ ነበር፤ በግብጽና በኢትዮጵያ ላይ የሚደርስባቸውም ምልክት ይኸው ነው።
4
የአሦር ንጉሠ ነገሥት ለግብጻውያን ኀፍረት ይሆን ዘንድ መቀመጫዎቻቸው ሳይሸፈኑ ወጣቶችም ሆኑ ሽማግሌዎች ዕራቊታቸውንና ባዶ እግራቸውን ሆነው ግብጾችንና ኢትዮጵያውያንን በምርኮ ይመራቸዋል።
5
በኢትዮጵያ የሚተማመኑና በግብጽም የሚመኩ ሁሉ ግራ ተጋብተው ተስፋ ይቈርጣሉ።
6
በዚያን ጊዜ በባሕር ዳርቻ የሚኖሩ ሰዎች፦ ‘እኛን ከአሦር ንጉሠ ነገሥት ያድኑናል ብለን ተስፋ ያደረግንባቸውና ወደ እነርሱ የተጠጋንባቸው አገሮች ምን እንደ ደረሰባቸው ተመልከቱ! እኛማ እንዴት እናመልጣለን?’ ” ይላሉ።
← Chapter 19
Chapter 21 →