bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Ezekiel 35
Ezekiel 35
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
1
እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ተናገረኝ፦
2
“የሰው ልጅ ሆይ! ፊትህን ወደ ኤዶም ተራራ መልሰህ በሕዝቡም ላይ ትንቢት ተናገር፤
3
እኔ ልዑል እግዚአብሔር የምለውንም ሁሉ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘የኤዶም ሕዝብ ሆይ! እነሆ እኔ እናንተን እቃወማለሁ፤ ምድራችሁንም ባድማና ወና ላደርግ በእናንተ ላይ ተነሥቼአለሁ።
4
ከተሞቻችሁንም አፈራርሳለሁ፤ ምድራችሁንም ባድማ አደርጋታለሁ፤ ከዚያም በኋላ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንኩ ታውቃላችሁ።
5
“ ‘ለብዙ ጊዜ ከቈየው ጥላቻችሁ የተነሣ በኃጢአቱ ምክንያት በደረሰበት የመጨረሻ ቅጣትና በመከራው ጊዜ የእስራኤልን ሕዝብ ለሰይፍ አሳልፋችሁ ሰጣችሁ።
6
ስለዚህ እኔ ልዑል እግዚአብሔር ሕያው እንደ መሆኔ ለግድያ አዘጋጃችኋለሁ፤ ገዳይም ያሳድዳችኋል፤ ደም ማፍሰስን ስላልጠላችሁ ገዳይ ያሳድዳችኋል።
7
እኔ የኤዶምን ተራራማ አገር ባድማና ወና አደርጋለሁ፤ በዚያም በኩል ማንም ሰው እንዳያልፍ አደርጋለሁ፤
8
ተራራዎችን ሁሉ በተገደሉ ሰዎች ሬሳ እሸፍናለሁ፤ በጦርነት የተገደለውም ሬሳ ኰረብቶቻችሁና ሸለቆዎቻችሁን ወንዞቻችሁንም ሁሉ ይሸፍናል፤
9
እኔ ለዘለዓለሙ ምድራችሁን ባድማ አደርጋለሁ፤ ዳግመኛም በከተሞቻችሁ የሚኖር አይገኝም፤ በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንኩ ታውቃላችሁ።
10
“ ‘እኔ እግዚአብሔር እዚያ ያለሁ ብሆንም እንኳ ሁለቱን ሕዝቦች፥ ማለት ይሁዳንና እስራኤልን፥ እንዲሁም ምድራቸውን ጭምር የእናንተ አድርጋችሁ ለመውረስ አስባችሁ ነበር።
11
ስለዚህም እኔ ልዑል እግዚአብሔር ሕያው እንደ መሆኔ በሕዝቤ ላይ ባላችሁ ጥላቻ ምክንያት ያሳያችሁት ቊጣና ምቀኝነት ሁሉ ተገቢውን ቅጣት እሰጣችኋለሁ። እነርሱም እናንተን በምቀጣበት ጊዜ የምቀጣችሁ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን እንዲያውቁ አደርጋለሁ።
12
እነርሱ ባድማ የተደረጉ ስለ ሆነ በእኛ ቊጥጥር ሥር እንዲሆኑ ተሰጥተውናል’ ብላችሁ በእስራኤል ተራራዎች ላይ የተናገራችሁትን የንቀት ንግግር እኔ እግዚአብሔር የሰማሁ መሆኔን ወደፊት ታውቃላችሁ።
13
በእኔ ላይ መገዳደራችሁንና ያለ ገደብም በእኔ ላይ መናገራችሁን ሰምቼአለሁ።”
14
ስለዚህም እኔ ልዑል እግዚአብሔር የምለው ይህ ነው፦ “ዓለም ሁሉ ሲደሰት የእናንተን አገር ግን ባድማ አደርጋታለሁ።
15
የእስራኤል ምድር ባድማ በመሆኑ እንደ ተደሰታችሁ እኔም የሴኢርን ተራራና የኤዶምን ግዛት ሁሉ ባድማ አደርጋለሁ፤ ከዚያ በኋላ ሁሉም እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ያውቃል።”
← Chapter 34
Chapter 36 →