bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Ezekiel 28
Ezekiel 28
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
1
እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ተናገረኝ፥
2
“የሰው ልጅ ሆይ! ልዑል እግዚአብሔር ለጢሮስ ንጉሥ እንዲህ ይላል ብለህ ንገረው፦ ‘ልብህ ስለ ታበየ እኔ አምላክ ነኝ በባሕሩ መካከል በአማልክት ዙፋን ላይ እቀመጣለሁ ብለሃል። ምንም እንኳ አንተ በሐሳብህ አምላክ ነኝ ብትል ሰው ነህ እንጂ አምላክ አይደለህም።
3
ከዳንኤል ይበልጥ ጥበበኛ የሆንክ ይመስልሃል፤ ምንም ምሥጢር እንደማይሰወርብህም ታስባለህ፤
4
በእርግጥ በጥበብህና በብልኀትህ ብዙ ሀብት አግኝተሃል፤ በግምጃ ቤትህም ብዙ ወርቅና ብር አግበስብሰሃል።
5
በንግድ ሥራም ባሳየኸው ታላቅ ብልኀት ብዙ ሀብት አግኝተሃል፤ ከሀብትህም ብዛት የተነሣ ኲራት ተሰምቶሃል።’
6
“እንግዲህ እኔ ልዑል እግዚአብሔር የምለው ይህ ነው፤ ‘እንደ አምላክ ጥበበኛ ነኝ ብለህ በማሰብህ ምክንያት፥
7
በአንተ ላይ አደጋ የሚጥሉ ጨካኞች ጠላቶችን አመጣብሃለሁ፤ እነርሱ በጥበብህና በብልኀትህ ያገኘኸውንና ያከማቸኸውን ያማረ ነገር ሁሉ ያጠፋሉ።
8
አንተን ወደ ጥልቁ ጒድጓድ ይጥሉሃል፤ በባሕሩም መካከል አሠቃቂ የሆነ ሞት ትሞታለህ።
9
ታዲያ ሊገድሉህ በሚመጡበት ጊዜ አሁንም ራስህን እንደ አምላክ ትቈጥር ይሆን? በገዳዮችህ እጅ ወድቀህ ስትገኝ ሰው እንጂ አምላክ ያለመሆንህ ይታወቃል።
10
በውጪ አገር ሰዎች እጅ በእግዚአብሔር የማያምኑ ሰዎችን ሞት ትሞታለህ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።’ ”
11
እግዚአብሔር እንዲህ ሲል እንደገና ተናገረኝ፦
12
“የሰው ልጅ ሆይ! የጢሮስ ንጉሥ ስለሚገጥመው መጥፎ ዕድል ሙሾ አውጣ፤ እኔ ልዑል እግዚአብሔር የምለውንም እንዲህ ብለህ ንገረው፦ ‘በጥበብ የተሞላህና እጅግ መልከ ቀና በመሆንህ የፍጹምነት ምሳሌ ነበርክ።
13
የእግዚአብሔር የአትክልት ቦታ በሆነችው በዔደን ውስጥ ትኖር ነበር፤ ሰርድዮን፥ ዐልማዝ፥ ቢረሌ፥ መረግድ፥ ኢያሰጲድ፥ ሰንፔርና በሉር ተብለው በሚጠሩ የከበሩ ድንጋዮች ያጌጠ የወርቅ ልብስ ትለብስ ነበር፤ ከተፈጠርክበት ጊዜ አንሥቶ ይህ ሁሉ ነበረህ።
14
አንተን እንደ ጠባቂ ኪሩብ አድርጌ በመሾም በዚያ መደብኩህ፤ በተቀደሰው ተራራዬ ላይ ትኖር ነበር፤ እጅግ በሚያብረቀርቁ የከበሩ ድንጋዮች መካከል ትመላለስ ነበር።
15
ከተፈጠርክበት ጊዜ አንሥቶ ክፋት ማድረግ እስከ ጀመርክበት ጊዜ ድረስ አካሄድህ ፍጹም ነበር፤
16
በመግዛትና በመሸጥ ተግባር ትጣደፍ ነበር፤ ይህም ሁሉ ወደ ግፍ ሥራና ወደ ኃጢአት መራህ፤ በዚህም ምክንያት የተቀደሰውን ተራራዬን ለቀህ እንድትወጣ አስገደድኩህ፤ ከነዚያ ከሚያብረቀርቁ የከበሩ ድንጋዮች መካከል ጠባቂው ኪሩብ እያባረረ አስወጣህ።
17
መልከ ቀና በመሆንህ እጅግ ታብየህ ነበር፤ ክብር በመፈለግህም ጥበብን አቃለልክ፤ ከዚህም የተነሣ አምዘግዝጌ ወደ መሬት ጣልኩህ፤ ለሌሎች ነገሥታትም የመቀጣጫ ምልክት አደረግሁህ።
18
በመግዛትና በመሸጥ ከፈጸምከው በደል የተነሣ የአምልኮ ስፍራዎችህ ሁሉ ረከሱ፤ ስለዚህ በከተማይቱ የሰደድ እሳት እንዲነሣ አድርጌ በሙሉ አቃጠልኳት፤ አሁን ወደ አንተ የሚመለከቱ ሁሉ ዐመድ ብቻ መሆንክን ያያሉ፤
19
እነሆ ጠፋህ! ለዘለዓለምም አትገኝም፤ ያውቁህ የነበሩ አገሮች ሁሉ ተሸብረዋል፤ በአንተ ላይ የደረሰው መጥፎ ዕድል እንዳይገጥማቸውም ፈርተዋል።’ ”
20
እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦
21
“የሰው ልጅ ሆይ! ፊትህን ወደ ሲዶና መልሰህ በእርስዋ ላይ ትንቢት ተናገር፤
22
ለሕዝብዋም ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል በላቸው፦ እኔ በእናንተ ላይ ተነሥቼአለሁ፤ በእናንተ ላይ በማደርገው ድርጊት ሕዝቦች ያመሰግኑኛል፤ ፍርዴን ተግባራዊ በማደርግበትና ቅድስናዬን በምገልጥበት ጊዜ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ያውቃሉ።
23
መቅሠፍቴን በእናንተ ላይ አመጣለሁ፤ በየመንገዱም ደም እንዲፈስስ አደርጋለሁ፤ በየአቅጣጫው በሚነሣባችሁ ጦርነት ምክንያት በመካከላችሁ ሰዎች ይገደላሉ፤ ሕዝቦችም እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ያውቃሉ።”
24
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በንቀት ከሚመለከትዋት፥ በዙሪያዋ ካሉ አገሮች ሁሉ እንደ እሾኽና አሜከላ በመሆን እስራኤልን የሚጐዳ ከእንግዲህ ወዲህ ማንም አይኖርም። እኔም ልዑል እግዚአብሔር እንደ ሆንኩ ያውቃሉ።”
25
ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እስራኤላውያን ከተበታተኑበት ከተለያዩ አሕዛብ መካከል በምሰበሰብበት ጊዜና ሌሎች ሕዝቦች እያዩ ቅድስናዬን በሕዝቤ መካከል በምገልጥበት ጊዜ ተመልሰው ለአገልጋዬ ለያዕቆብ በሰጠሁት በገዛ ምድራቸው ይኖራሉ።
26
እዚያ ያለ ስጋት ይኖራሉ፤ ቤቶችን ይሠራሉ፤ ወይንም ይተክላሉ፤ በንቀት ይመለከቱአቸው የነበሩትን ጐረቤቶቻቸውን ሁሉ እቀጣለሁ፤ እስራኤላውያን ግን ያለ ስጋት በመተማመን ይኖራሉ፤ በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር አምላካቸው እንደ ሆንኩ ያውቃሉ።”
← Chapter 27
Chapter 29 →