bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Ezekiel 15
Ezekiel 15
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
1
እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦
2
“የሰው ልጅ ሆይ! የወይን ግንድ ከሌሎች ዛፎች ግንድ ቅርንጫፎች ከዱር ዛፎች ቅርንጫፍ በምን ይበልጣል?
3
አንድ ነገር እንኳ ለመሥራት ይጠቅማልን? የዕቃ መስቀያ ኩላብ እንኳ ከእርሱ ሊሠራ ይችላልን?
4
የእሳት ማቀጣጠያ ከመሆን በቀር ሌላ ጥቅም የለውም፤ ጫፎቹ ነደው መካከሉ ካረረ በኋላ በእርሱ አንድ ነገር እንኳ መሥራት ይቻላልን?
5
ከመቃጠሉ በፊት እንኳ ዋጋቢስ ከነበረ አሁንማ እሳቱ ካቃጠለውና ካሳረረው በኋላ የባሰውን ጥቅም የሌለው ይሆናል።”
6
ስለዚህ ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በዱር ካሉ ዛፎች መካከል የወይንን ግንድ ለማገዶ እንዳደረግሁት የኢየሩሳሌምን ሕዝብ እንዲሁ አደርገዋለሁ።
7
እቈጣቸዋለሁ፤ ምንም እንኳ ለጊዜው ከእሳቱ ቢያመልጡ እሳቱ ግን ይበላቸዋል፤ እነርሱንም በምትቈጣበት ጊዜ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ።
8
እነርሱ በእኔ መታመናቸውን ትተዋል፤ እኔም አገራቸው ምድረ በዳ እንድትሆን አደርጋለሁ፤ ይላል ልዑል እግዚአብሔር።”
← Chapter 14
Chapter 16 →