bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Ecclesiastes 11
Ecclesiastes 11
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
1
እንጀራህን በውሃ ላይ ጣል፤ ከብዙ ቀንም በኋላ መልሰህ ታገኘዋለህ።
2
ወደ ፊት በዓለም ላይ ምን ዐይነት ክፉ ነገር እንደሚመጣ አታውቅም፤ ስለዚህ ያለህን ሀብት በሰባት ወይም በስምንት ቦታ ከፋፍለህ አኑር።
3
ደመና ብዙ ውሃ ባዘለ ጊዜ በምድር ላይ ያዘንበዋል፤ ዛፍ ወደ ደቡብም ሆነ ወደ ሰሜን ቢወድቅ በዚያው በወደቀበት ስፍራ ይኖራል።
4
ነፋስን የሚጠብቅ አይዘራም፤ ደመናን የሚመለከት አያጭድም።
5
የነፋስን አካሄድና የሰውም ሕይወት አፈጣጠር በእናቱ ማሕፀን እንዴት እንደሚጀመር እንደማታውቅ የሁሉ ነገር ፈጣሪ እግዚአብሔር ሥራውን እንዴት እንደሚያከናውን ማወቅ አትችልም።
6
ጧትም ሆነ ማታ ዘር መዝራትህን አታቋርጥ፤ ሁሉም ይበቅል ወይም አይበቅል እንደ ሆነ የትኛው አዘራር እንደሚሻል ለይተህ ማወቅ አይቻልህም።
7
ብርሃን ታይቶ አይጠገብም፤ ስለዚህ የቀንን ብርሃን እያዩ መደሰት መልካም ነው።
8
ሰው የቱንም ያኽል ብዙ ዓመት ቢኖር በዚያው በተሰጠው በዕድሜው ዘመን ሁሉ ደስ ሊለው ይችላል፤ ሆኖም የዚህ ዓለም ነገር ሁሉ ከንቱ መሆኑንና ወደፊት የሚመጣበትም የጨለማ ዘመን ዘለዓለማዊ እንደ ሆነ አይዘንጋ።
9
ወጣት ሆይ! ወጣትነት እጅግ ግሩም ስለ ሆነ በወጣትነትህ ዘመን ደስ ይበልህ፤ በልብህም ሐሤት አድርግ፤ ዐይንህ የሚያየውንና ልብህ የሚመኘውን ሁሉ ፈጽም፤ ሆኖም ስለዚህ ነገር ሁሉ እግዚአብሔር ወደ ፍርድ እንደሚያመጣህ ዕወቅ።
10
የወጣትነትና የብርቱ ጐልማሳነት ጊዜ ቶሎ ስለሚያልፍ ሐዘንን ከልብህ፥ ጭንቀትንም ከአእምሮህ አስወግድ።
← Chapter 10
Chapter 12 →