bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
2 Chronicles 33
2 Chronicles 33
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
1
ምናሴ በይሁዳ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ዐሥራ ሁለት ዓመት ነበር፤ መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ኀምሳ አምስት ዓመት ገዛ፤
2
እስራኤላውያን ወደ ተስፋይቱ አገር በሚገቡበት ጊዜ፥ እግዚአብሔር ከፊታቸው ነቃቅሎ ያጠፋቸውን የአሕዛብን አሳፋሪ ልማድ በመከተል፥ ምናሴ የሠራው ኃጢአት እግዚአብሔርን አሳዘነ፤
3
ምናሴ አባቱ ሕዝቅያስ አፈራርሶአቸው የነበሩትን የአሕዛብ የማምለኪያ ስፍራዎች እንደገና ሠራ፤ ባዓል ተብሎ ለሚጠራው ባዕድ አምላክ መሠዊያዎችን፥ አሼራ ተብላ ለምትጠራው ሴት አምላክ ምስሎችን አቆመ፤ የሰማይ ከዋክብትንም አመለከ፤
4
እግዚአብሔር ለዘለዓለም ስሙ ይጠራበታል ባለው ስፍራ፥ ማለትም በኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ ውስጥ አረማዊ መሠዊያዎችን ተከለ፤
5
በሁለቱም የቤተ መቅደሱ አደባባዮች የሰማይ ከዋክብት የሚመለኩባቸውን መሠዊያዎች ሠራ፤
6
የገዛ ወንዶች ልጆቹንም በሂኖም ሸለቆ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ አቀረበ፤ እርሱም ራሱ ሟርተኛና አስማተኛ ሆኖ፥ ከጠንቋዮችና ከሙታን ጠሪዎች ምክርን ይጠይቅ ነበር፤ በዚህም ሁሉ አድራጎቱ ታላቅ ኃጢአት ስለ ሠራ፥ እግዚአብሔርን አስቈጣ።
7
በቤተ መቅደስም ውስጥ የጣዖት ምስልን አቆመ፤ ይህም ቤተ መቅደስ እግዚአብሔር ለዳዊትና ለልጁ ለሰሎሞን “ይህ በኢየሩሳሌም የሚገኘው ቤተ መቅደስ ስሜ እንዲጠራበት ከዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ግዛት ሁሉ የመረጥኩት የተቀደሰ ስፍራ ነው፤
8
እስራኤላውያን በሙሴ አማካይነት ያዘዝኳቸውን ሕጌን፥ ሥርዓቴንና ድንጋጌዬን ሁሉ በጥንቃቄ ቢጠብቁ ለቀድሞ አባቶቻቸው ከሰጠኋቸው ምድር እንደገና እንዲፈናቀሉ አላደርግም።
9
ምናሴ የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ሕዝብ፥ የእስራኤል ልጆች ወደ ተስፋይቱ አገር በሚገቡበት ጊዜ፥ እግዚአብሔር ከፊታቸው እንዲባረሩ ያደረጋቸው ሕዝቦች ካደረጉት ይበልጥ የከፋ ኃጢአት እንዲሠሩ አደረጋቸው።”
10
እግዚአብሔር ምናሴንና ሕዝቡን በብርቱ ያስጠነቀቃቸው ቢሆንም እንኳ እነርሱ መስማትን እምቢ አሉ፤
11
ስለዚህም የአሦር ሠራዊት ይሁዳን እንዲወር እግዚአብሔር ፈቀደ፤ ሠራዊቱም ምናሴን ማርኮ በአፍንጫው ሥናጋ በማግባት በሰንሰለት አስሮ ወደ ባቢሎን ወሰደው።
12
ምናሴ ሥቃይ በበዛበት ጊዜ ራሱን በትሕትና በማዋረድ ወደ አምላኩ ወደ እግዚአብሔር ተመለሰ፤ የእግዚአብሔርንም ርዳታ ለመነ፤
13
እግዚአብሔርም የምናሴን ጸሎት ሰማ፤ ወደ ኢየሩሳሌምም ተመልሶ እንደገና እንዲገዛ ፈቀደለት፤ በዚህም ምናሴ እግዚአብሔር እውነተኛ አምላክ መሆኑን ተገነዘበ።
14
ከዚህ በኋላ ምናሴ በዳዊት ከተማ በስተ ምሥራቅ በኩል የሚገኘውን የውጪ ቅጽር ቁመት ከፍ አድርጎ ሠራ፤ ይህም ቅጽር በሸለቆው ውስጥ ከግዮን ምንጭ በስተ ምዕራብ በኩል አንሥቶ፥ በስተ ሰሜን እስከ ዓሣ ቅጽር በር የሚደርስ ሲሆን፥ በከተማይቱ አጠገብ የሚገኘውን ዖፌል ተብሎ የሚጠራውን ስፍራ የሚያጠቃልል ነው፤ እንዲሁም ምናሴ በተመሸጉት የይሁዳ ከተሞች ሁሉ፥ ለእያንዳንዳቸው አንዳንድ የክፍለ ጦር አዛዥ መደበላቸው።
15
ምናሴ ባዕዳን አማልክትንና እርሱ ራሱ በዚያ አቁሞት የነበረውን የጣዖት ምስል ከቤተ መቅደስ አወጣ፤ እንዲሁም በኢየሩሳሌም ቤተ መቅደሱ በቆመበት ኰረብታና በሌሎችም ስፍራዎች ላይ የነበሩትን የጣዖቶች መሠዊያዎች ሁሉ አስወገደ፤ እነዚህንም ሁሉ አንሥቶ፥ ከከተማይቱ ውጪ ጣላቸው፤
16
የእግዚአብሔርንም መሠዊያ በማደስ በላዩ ላይ የኅብረት መሥዋዕትና የምስጋና መባን አቀረበ፤ የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን ያመልኩም ዘንድ መላውን የይሁዳ ሕዝብ አዘዘ።
17
ሕዝቡ በሌሎቹ ኰረብታማ የማምለኪያ ስፍራዎች ላይ መሥዋዕት ማቅረባቸውን ቢቀጥሉም እንኳ መሥዋዕቱን የሚያቀርቡት ለእግዚአብሔር ብቻ ነበር።
18
ምናሴ ያደረገው ሌላ ነገር ሁሉ፥ ለአምላኩ ለእግዚአብሔር ያቀረበው ጸሎት፥ ነቢያት በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ስም ለምናሴ የተናገሩአቸው ቃላት ጭምር፥ በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግበው ይገኛሉ።
19
ንጉሥ ምናሴ ወደ እግዚአብሔር ያቀረበው ጸሎትና፥ እግዚአብሔርም ለጸሎቱ የሰጠው መልስ፥ ተጸጽቶ ንስሓ ከመግባቱ በፊት ያደረገው ኃጢአት ሁሉ፥ ማለትም የፈጸመው ልዩ ልዩ ክፋት፥ እርሱ ራሱ የሠራቸው የአሕዛብ ማምለኪያ ስፍራዎችና አሼራ ተብላ የምትጠራው ሴት አምላክ ምስሎች፥ ያመልካቸው የነበሩ ጣዖቶች ሁሉ፥ በነቢያት የታሪክ መጻሕፍት ውስጥ ተመዝግበው ይገኛሉ።
20
ምናሴ ሞተ፤ በቤተ መንግሥቱም አጠገብ በሚገኘው ስፍራ ተቀበረ፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ልጁ አሞን ነገሠ።
21
አሞን ዕድሜው ኻያ ሁለት ዓመት ሲሆነው በይሁዳ ላይ ነገሠ፤ መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ሁለት ዓመት ገዛ፤
22
እርሱም እንደ አባቱ እንደ ምናሴ ኃጢአት በመሥራት እግዚአብሔርን አሳዘነ፤ አባቱ ያመልካቸው የነበሩትንም ጣዖቶች አመለከ፤ መሥዋዕትንም አቀረበላቸው።
23
አባቱ እንዳደረገው ሁሉ ራሱን በትሕትና ዝቅ አድርጎ በማዋረድ ወደ እግዚአብሔር አልተመለሰም፤ እንዲያውም ከአባቱ ይበልጥ የከፋ ኃጢአት ሠራ።
24
የአሞን ባለሟሎች የሆኑት ባለሥልጣኖች በእርሱ ላይ በማሤር በቤተ መንግሥቱ ውስጥ ገደሉት፤
25
የይሁዳም ሕዝብ የአሞንን ገዳዮች ገድለው በእርሱ እግር ልጁን ኢዮስያስን አነገሡ።
← Chapter 32
Chapter 34 →