bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
1 Thessalonians 3
1 Thessalonians 3
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
1
ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲህ መታገሥ ባለመቻላችን በአቴና ብቻችንን መቅረት መልካም ሆኖ ታየን።
2
ወንድማችንንና የእግዚአብሔር አገልጋይ የሆነውን፥ የክርስቶስን መልካም ዜና በማብሠር የሥራ ጓደኛችንን ጢሞቴዎስን ልከንላችኋል፤ የላክንላችሁም እንዲያጸናችሁና በእምነት እንድትበረቱ እንዲመክራችሁ ነው፤
3
ይህም በደረሰባችሁ መከራ እንዳትናወጡ ያደርጋችኋል፤ ይህ መከራ ለእኛ የተወሰነልን ዕጣ መሆኑን እናንተ ራሳችሁ ታውቃላችሁ።
4
እንዲያውም ከእናንተ ጋር በነበርንበት ጊዜ መከራ እንደሚደርስብን አስቀድመን እንነግራችሁ ነበር፤ እንደምታውቁትም መከራው ደርሶብናል፤
5
በዚህ ምክንያት ከእንግዲህ ወዲህ በትዕግሥት መጠበቅ ባለመቻሌ ስለ እምነታችሁ ማወቅ ፈልጌ ጢሞቴዎስን ወደ እናንተ ላክሁት፤ እርሱን የላክሁትም ምናልባት ፈታኙ በአንድ መንገድ ፈትኖአችሁ ይሆናል፤ ሥራችንም ከንቱ ሆኖ ቀርቶአል በማለት ፈርቼ ነው።
6
አሁን ግን ጢሞቴዎስ ከእናንተ ዘንድ ወደ እኛ መጥቶ ስለ እምነታችሁና ስለ ፍቅራችሁ ደስ የሚያሰኝ ዜና ነገረን፤ እንዲሁም እናንተ ዘወትር በመልካም እንደምታስታውሱንና እኛ እናንተን ለማየት የምንናፍቃችሁን ያኽል እናንተም እኛን ለማየት እንደምትናፍቁ ነገረን።
7
ስለዚህ ወንድሞች ሆይ፥ እኛ የምንገኘው በችግርና በመከራ ውስጥ ቢሆንም እንኳ በእምነታችሁ ምክንያት በእናንተ ተጽናንተናል።
8
የእናንተ በጌታ ኢየሱስ ጸንቶ መኖር ለእኛ ሕይወታችን ነው።
9
እነሆ፥ አሁን ስለ እናንተ ምስጋና እናቀርባለን፤ በእናንተም ምክንያት በእርሱ ፊት ስላለን ደስታ እግዚአብሔርን እናመሰግናለን።
10
ሌሊትና ቀን በብርቱ የምንጸልየው በዐይነ ሥጋ እንድናያችሁና በእምነታችሁ የጐደለውን ለመሙላት እንድንችል ነው።
11
አሁንም አምላካችንና አባታችን ራሱ ጌታችን ኢየሱስም ወደ እናንተ እንድንመጣ መንገዳችንን ያቅናልን።
12
እኛ እንደምናፈቅራችሁ ጌታ እርስ በርስና ለሌሎችም ሁሉ ያላችሁ ፍቅር እንዲያድግና እንዲበዛ ያድርግላችሁ፤
13
በዚህ ዐይነት ጌታችን ኢየሱስ ከቅዱሳኑ ሁሉ ጋር በሚመጣበት ጊዜ በአምላካችንና በአባታችን ፊት ልባችሁ ነቀፋ የሌለበትና ቅዱስ እንዲሆን ያበረታችኋል።
← Chapter 2
Chapter 4 →