bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Zechariah 9
Zechariah 9
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
የእግዚአብሔር ቃል ንግር በሴድራክ ምድር ላይ ይወርድበታል፤ በደማስቆም ላይ ያርፍበታል፤ የሰዎችና የእስራኤል ነገዶች ሁሉ ዐይን፣ በእግዚአብሔር ላይ ዐርፏልና።
2
ደግሞም በአዋሳኟ በሐማት፣ ጥበበኞች ቢሆኑም እንኳ በጢሮስና በሲዶና ላይ ያርፍባቸዋል።
3
ጢሮስ ለራሷ ምሽግ ሠርታለች፤ ብሩን እንደ ዐፈር ወርቁንም እንደ መንገድ ላይ ትቢያ ቈልላለች።
4
ጌታ ግን ሀብቷን ይወስዳል፤ በባሕር ያላትንም ኀይል ይደምስሳል፤ እርሷም በእሳት ፈጽማ ትጠፋለች።
5
አስቀሎና አይታ ትርዳለች፤ ጋዛ በሥቃይ ትቃትታለች፤ አቃሮናም እንደዚሁ ትሠቃያለች፤ ተስፋዋ ይመነምናልና። ጋዛ ንጉሥዋን ታጣለች፤ አስቀሎናም ባድማ ትሆናለች።
6
ድብልቅ ሕዝቦች አዛጦንን ይይዛሉ፤ የፍልስጥኤማውያንንም ትምክሕት እቈርጣለሁ።
7
ደሙን ከአፋቸው፣ የተከለከለውንም ምግብ ከመንጋጋቸው አወጣለሁ። የተረፉት ለአምላካችን ይሆናሉ፤ በይሁዳም አለቆች ይሆናሉ፤ አቃሮንም እንደ ኢያቡሳዊ ይሆናል።
8
እኔ ግን ቤቴን ከዘራፊ ኀይሎች እጠብቃለሁ፤ ጨቋኝ ከእንግዲህ ሕዝቤን አይወርስም፤ አሁን ነቅቼ እጠብቃለሁና።
9
አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፤ እጅግ ደስ ይበልሽ፤ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፤ እልል በዪ፤ እነሆ፤ ጻድቁና አዳኙ ንጉሥሽ ፣ ትሑት ሆኖ፣ በአህያ ላይ ተቀምጦ፣ በአህያ ግልገል፣ በውርንጫዪቱ ላይ ሆኖ ወደ አንቺ ይመጣል።
10
ሠረገሎችን ከኤፍሬም፣ የጦር ፈረሶችን ከኢየሩሳሌም እወስዳለሁ፤ የጦርነቱም ቀስት ይሰበራል፤ ሰላምን ለአሕዛብ ያውጃል፤ ግዛቱም ከባሕር እስከ ባሕር፣ ከወንዙም እስከ ምድር ዳር ድረስ ይዘረጋል።
11
ለአንቺ ደግሞ፣ ከአንቺ ጋር ከገባሁት የደም ቃል ኪዳን የተነሣ፣ እስረኞችሽን ውሃ ከሌለበት ጕድጓድ ነጻ እለቅቃቸዋለሁ።
12
እናንት በተስፋ የምትኖሩ እስረኞች፤ ወደ ምሽጎቻችሁ ተመለሱ፤ አሁንም ቢሆን ሁለት ዕጥፍ አድርጌ እንደምመልስላችሁ እናገራለሁ።
13
ቀስቴን እንደ ገተርሁ፣ ይሁዳን እገትረዋለሁ፤ ኤፍሬምንም ፍላጻ አደርገዋለሁ። ጽዮን ሆይ፤ ልጆችሽን አስነሣለሁ፤ ግሪክ ሆይ፤ በአንቺ ልጆች ላይ ይነሣሉ፤ እንደ ተዋጊ ሰይፍም አደርግሻለሁ።
14
እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ ይገለጣል፤ ፍላጻውም እንደ መብረቅ ይወጣል፤ ጌታ እግዚአብሔር መለከት ይነፋል፤ በደቡብም ዐውሎ ንፋስ ውስጥ ይጓዛል፤
15
እግዚአብሔር ጸባኦትም ይከልላቸዋል፤ ጠላቶቻቸውን ይደመስሳሉ፤ በድንጋይ ወንጭፍም ያሸንፋሉ፤ ይጠጣሉ፤ በወይን ጠጅ እንደ ሰከረ ሰው ይጮኻሉ፤ የመሠዊያውን ማእዘኖች ለመርጨት፣ እንደ ተዘጋጀ ዕቃ ፣ እነርሱም እንደዚሁ ተሞልተዋል።
16
ሕዝቡን የራሱ መንጋ አድርጎ በዚያ ቀን አምላካቸው እግዚአብሔር ያድናቸዋል። በአክሊል ላይ እንዳለ ዕንቍ፣ በገዛ ምድሩ ላይ ያብለጨልጫሉ።
17
እንዴት ውብና አስደናቂ ይሆናሉ፤ እህል ጕልማሶችን፣ አዲስ የወይን ጠጅም ቈነጃጅትን ያሳምራል።
← Chapter 8
Chapter 10 →