bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Zechariah 7
Zechariah 7
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
ዳርዮስ በነገሠ በአራተኛው ዓመት፣ ካሴሉ በተባለው በዘጠነኛው ወር፣ በአራተኛው ቀን የእግዚአብሔር ቃል ወደ ዘካርያስ እንዲህ ሲል መጣ፤
2
የቤቴል ሰዎች እግዚአብሔርን ለመለመን ሳራሳርንና ሬጌሜሌክን አብረዋቸው ከነበሩት ሰዎች ጋር ላኩ፤
3
እነርሱም የእግዚአብሔር ጸባኦት ቤት ካህናትና ነቢያት፣ “ብዙ ዓመት እንዳደረግሁት፣ በአምስተኛው ወር ማዘንና መጾም ይገባኛልን?” ብለው ጠየቁ።
4
ከዚያም የእግዚአብሔር ጸባኦት ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤
5
“የምድሩን ሕዝብ ሁሉና ካህናቱን እንዲህ በላቸው፤ ‘ባለፉት ሰባ ዓመታት በአምስተኛውና በሰባተኛው ወር የጾማችሁትና ያዘናችሁት በርግጥ ለእኔ ነበርን?
6
ትበሉና ትጠጡ የነበረውስ ለራሳችሁ አይደለምን?
7
ኢየሩሳሌምና በዙሪያዋ ያሉ ከተሞች በሰላምና በብልጽግና ላይ ሳሉ፣ የደቡብና የምዕራብ ኰረብቶች ግርጌ የሰው መኖሪያም በነበሩበት ጊዜ፣ እግዚአብሔር በቀደሙት ነቢያት የተናገረው ቃል ይህ አልነበረምን?’ ”
8
የእግዚአብሔር ቃል እንደ ገና ወደ ዘካርያስ እንዲህ ሲል መጣ፤
9
“ እግዚአብሔር ጸባኦት እንዲህ ይላል፤ ‘እውነተኛ ፍትሕ አስፍኑ፣ እርስ በርሳችሁ ምሕረትና ርኅራኄን አድርጉ፤
10
መበለቲቱን ወይም ድኻ ዐደጉን፣ መጻተኛውን ወይም ድኻውን አታስጨንቁ፤ በልባችሁም አንዳችሁ በአንዳችሁ ላይ ክፉ አታስቡ።’
11
“እነርሱ ግን መስማት አልፈለጉም፤ በእልኸኝነት ጀርባቸውን አዞሩ፤ ጆሯቸውንም ደፈኑ።
12
ልባቸውን እንደ ባልጩት አጠነከሩ፤ እግዚአብሔር ጸባኦት በቀደሙት ነቢያት በኩል በመንፈሱ የላከውን ቃል ወይም ሕግ አልሰሙም፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ጸባኦት እጅግ ተቈጣ።
13
“ ‘ስጠራቸው አልሰሙም፤ ስለዚህ ሲጠሩኝ አልሰማም’ ይላል እግዚአብሔር ጸባኦት።
14
‘በማያውቋቸው በባዕዳን አሕዛብ መካከል በዐውሎ ነፋስ በተንኋቸው፤ ከእነርሱ በኋላ ማንም እስከማይመጣባትና እስከማይሄድባት ድረስ ምድሪቱ ባድማ ሆነች፤ መልካሚቱን ምድር ባድማ ያደረጓት በዚህ ሁኔታ ነው።’ ”
← Chapter 6
Chapter 8 →