bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Zechariah 13
Zechariah 13
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
“በዚያ ቀን የዳዊትን ቤትና የኢየሩሳሌምን ነዋሪዎች ከኀጢአትና ከርኩሰት የሚያነጻ ምንጭ ይከፈታል።
2
“በዚያ ቀን የጣዖታትን ስም ከምድሪቱ አጠፋለሁ፤ ከእንግዲህም አይታሰቡም” ይላል እግዚአብሔር ጸባኦት። “ነቢያትንና ርኩስ መንፈስን ከምድሪቱ አስወግዳለሁ።
3
ማንም ትንቢት ቢናገር ወላጅ አባትና እናቱ፣ ‘ በእግዚአብሔር ስም ሐሰት ተናግረሃልና ሞት ይገባሃል’ ይሉታል። ትንቢት ሲናገርም የገዛ ወላጆቹ ይወጉታል።
4
“በዚያን ቀን እያንዳንዱ ነቢይ ስለሚናገረው የትንቢት ራእይ ያፍራል፤ ለማታለልም የነቢያትን ጠጕራም ልብስ አይለብስም።
5
እርሱም፣ ‘እኔ ገበሬ እንጂ ነቢይ አይደለሁም፤ ከልጅነቴ ጀምሮ ኑሮዬ የተመሠረተውም በዕርሻ ላይ ነው’ ይላል።
6
አንድ ሰው፣ ‘ይህ በሰውነትህ ላይ ያለው ቍስል ምንድን ነው?’ ብሎ ቢጠይቀው፣ ‘በባልንጀሮቼ ቤት ሳለሁ የቈሰልሁት ነው’ ይላል።”
7
እግዚአብሔር ጸባኦት እንዲህ ይላል፤ “ሰይፍ ሆይ፤ በእረኛዬ፣ በቅርብ ወዳጄ ላይ ንቃ! እረኛውን ምታ፣ በጎቹ ይበተናሉ፤ እኔም ክንዴን ወደ ታናናሾቹ አዞራለሁ።”
8
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “የምድር ሁሉ፣ ሁለት ሦስተኛው ተመትቶ ይጠፋል፤ አንድ ሦስተኛው ግን በውስጡ ይቀራል፤
9
ይህን አንድ ሦስተኛውን ክፍል ወደ እሳት አመጣለሁ፤ እንደ ብር አነጥራቸዋለሁ፤ እንደ ወርቅም እፈትናቸዋለሁ፤ እነርሱ ስሜን ይጠራሉ፤ እኔም እመልስላቸዋለሁ፤ እኔም፣ ‘ሕዝቤ ናቸው’ እላለሁ፤ እነርሱም፣ ‘ እግዚአብሔር አምላካችን ነው’ ይላሉ።”
← Chapter 12
Chapter 14 →