bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Song of Solomon 4
Song of Solomon 4
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
ውዴ ሆይ፤ እንዴት ውብ ነሽ! እንዴትስ ያለሽ ቈንጆ ነሽ ከመሸፈኛሽ ውስጥ ያሉት ዐይኖችሽ እንደ ርግብ ዐይኖች ናቸው፤ ጠጕርሽም ከገለዓድ ተራራ እንደሚወርድ፣ የፍየል መንጋ ነው።
2
ጥርሶችሽ ወዲያው ተሸልተው፣ ከመታጠቢያ እንደ ወጡ የበግ መንጋ ናቸው፤ ሁሉም መንታ መንታ የወለዱ፣ ከመካከላቸውም መካን የሌለባቸው ናቸው።
3
ከንፈሮችሽ ቀይ የሐር ፈትል ይመስላሉ፤ አፍሽም ውብ ነው፤ ከመሸፈኛሽ ውስጥ ያሉት ጕንጮችሽ፣ ለሁለት የተከፈለ ሮማን ይመስላሉ።
4
ዐንገትሽ አምሮ የተሠራውን በላዩም የጦረኞች ጋሻዎች ሁሉ ያሉበትን፣ ሺሕ ጋሻዎች የተንጠለጠሉበትን፣ የዳዊትን የመጠበቂያ ማማ ይመስላል።
5
ሁለቱ ጡቶችሽ መንታ ሆነው የተወለዱ፣ በውብ አበቦች መካከልም የተሰማሩ፣ ሁለት የሚዳቋ ግልገሎችን ይመስላሉ።
6
ጎሕ ከመቅደዱ በፊት፣ ጥላውም ሳይሸሽ፣ ወደ ከርቤ ተራራ፣ ወደ ዕጣኑም ኰረብታ እወጣለሁ።
7
ውዴ ሆይ፤ ሁለንተናሽ ውብ ነው፤ እንከንም አይወጣልሽም።
8
ሙሽራዬ ሆይ፤ ከሊባኖስ አብረሽኝ ነዪ፤ አዎን ከሊባኖስ አብረሽኝ ነዪ፤ ከአንበሶች ዋሻ፣ ከነብሮች ተራራ፣ ከኤርሞን ራስ፣ ከሳኔር ጫፍ፣ ከአማና ዐናት ውረጂ።
9
እኅቴ ሙሽራዬ፣ ልቤን ሰርቀሽዋል፤ በአንድ አፍታ እይታሽ፣ ከሐብልሽም በአንዱ ዕንቍ፣ ልቤን ሰርቀሽዋል።
10
እኅቴ ሙሽራዬ፣ ፍቅርሽ እንዴት ደስ ያሰኛል! ፍቅርሽ ከወይን ጠጅ ይልቅ ምንኛ የሚያረካ ነው፤ የሽቱሽም መዐዛ ከቅመም ሁሉ ይልቅ የቱን ያህል ይበልጥ!
11
ሙሽራዬ ሆይ፤ ከንፈሮችሽ የማር ወለላ ያንጠባጥባሉ፤ ከአንደበትሽም ወተትና ማር ይፈልቃል፤ የልብስሽም መዐዛ እንደ ሊባኖስ ሽታ ነው።
12
እኅቴ ሙሽራዬ፤ የታጠረ የአትክልት ቦታ፣ ዙሪያውን የተከበበ ምንጭ፣ የታተመም ፏፏቴ ነሽ።
13
ተክልሽ ሮማን፣ ምርጥ ፍሬዎች፣ ሄናና ናርዶስ ያሉበት ነው።
14
እንዲሁም ናርዶስና ቀጋ፣ ጠጅ ሣርና ቀረፋ፣ የተለያዩ የዕጣን ዛፎች፣ ከርቤና እሬት፣ ምርጥ ቅመሞች ሁሉ አሉበት።
15
አንቺ የአትክልት ቦታ ፏፏቴ፣ ከሊባኖስ የሚወርድ፣ የፈሳሽ ውሃ ጕድጓድ ነሽ።
16
የሰሜን ነፋስ ሆይ፤ ንቃ፤ የደቡብም ነፋስ ሆይ፤ ና! መዐዛው ያውድ ዘንድ፣ በአትክልት ቦታዬ ላይ ንፈስ፤ ውዴ ወደ አትክልት ቦታው ይግባ፤ ምርጥ ፍሬዎቹንም ይብላ።
← Chapter 3
Chapter 5 →