bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Psalms 91
Psalms 91
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
በልዑል መጠጊያ የሚኖር፣ ሁሉን በሚችል አምላክ ጥላ ሥር ያድራል።
2
እግዚአብሔርን ፣ “መጠጊያዬ፣ ምሽጌ፣ የምታመንብህ አምላኬ” እለዋለሁ።
3
እርሱ ከዐዳኝ ወጥመድ፣ ከአሰቃቂ ቸነፈር ያድንሃልና።
4
በላባዎቹ ይጋርድሃል፤ በክንፎቹ ሥር መሸሸጊያ ታገኛለህ፤ ታማኝነቱ ጋሻና መከታ ይሆንሃል።
5
የሌሊትን አስደንጋጭነት፣ በቀን የሚወረወረውንም ፍላጻ አትፈራም፤
6
በጨለማ የሚያደባ ቸነፈር፣ በቀትር ረፍራፊውም አያሠጋህም።
7
በአጠገብህ ሺሕ፣ በቀኝህም ዐሥር ሺሕ ይወድቃል፤ ወደ አንተ ግን አይቀርብም።
8
በዐይንህ ብቻ ትመለከታለህ፤ የክፉዎችንም መቀጣት ታያለህ።
9
እግዚአብሔርን መሸሸጊያ፣ ልዑልንም መጠጊያህ አድርገኸዋልና።
10
ክፉ ነገር አያገኝህም፤ መቅሠፍትም ወደ ድንኳንህ አይገባም፤
11
በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ፣ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዛቸዋልና።
12
እግርህ ከድንጋይ ጋር እንዳይጋጭ፣ በእጆቻቸው ወደ ላይ ያነሡሃል።
13
በአንበሳና በእፉኝት ላይ ትጫማለህ፤ ደቦሉን አንበሳና ዘንዶውን ትረግጣለህ።
14
“ወድዶኛልና እታደገዋለሁ፤ ስሜን ዐውቋልና እከልለዋለሁ።
15
ይጠራኛል፤ እመልስለታለሁ፤ በመከራው ጊዜ ከእርሱ ጋር እሆናለሁ፤ አድነዋለሁ፤ አከብረዋለሁ።
16
ረዥም ዕድሜን አጠግበዋለሁ፤ ማዳኔንም አሳየዋለሁ።”
← Chapter 90
Chapter 92 →