bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Psalms 88
Psalms 88
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
አዳኜ የሆንህ አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ በቀንና በሌሊት በፊትህ እጮኻለሁ።
2
ጸሎቴ በፊትህ ትድረስ፤ ጆሮህንም ወደ ጩኸቴ አዘንብል፤
3
ነፍሴ በመከራ ተሞልታለችና፤ ሕይወቴም ወደ ሲኦል ተቃርባለች።
4
ወደ ጕድጓድ ከሚወርዱት ጋር ተቈጠርሁ፤ ዐቅምም ዐጣሁ።
5
በሙታን መካከል እንደ ተጣሉ፣ ተገድለው በመቃብር ውስጥ እንደ ተጋደሙ፣ አንተ ከእንግዲህ እንደማታስባቸው፣ ከእጅህም ወጥተው እንደ ተወገዱ ሆንሁ።
6
በዐዘቅት ጥልቀት ውስጥ ጣልኸኝ፤ በጨለማ ጕድጓድ ውስጥ ከተትኸኝ።
7
የቍጣህ ክብደት በላዬ ዐርፏል፤ በማዕበልህም ሁሉ አጥለቅልቀኸኛል።
8
የሚቀርቡኝ ባልንጀሮቼን ከእኔ አራቅህ፤ እንዲጸየፉኝም አደረግህ፤ ተከብቤአለሁ፤ ማምለጥም አልችልም፤
9
ዐይኖቼም በሐዘን ፈዘዙ። እግዚአብሔር ሆይ፤ ዘወትር ወደ አንተ እጣራለሁ፤ እጆቼንም ወደ አንተ ዘረጋሁ።
10
ድንቅ ሥራህን ለሙታን ታሳያለህን? የሙታንስ መናፍስት ተነሥተው ያመሰግኑሃልን?
11
ምሕረትህ በመቃብር ውስጥ፣ ታማኝነትህስ እንጦርጦስ ይነገራልን?
12
ድንቅ ሥራህ በጨለማ ስፍራ፣ ጽድቅህስ በመረሳት ምድር ትታወቃለችን?
13
እግዚአብሔር ሆይ፤ እኔ ግን ትረዳኝ ዘንድ ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ በጧትም ጸሎቴን በፊትህ አደርሳለሁ።
14
እግዚአብሔር ሆይ፤ ለምን ታርቀኛለህ? ፊትህንስ ከእኔ ለምን ትሰውራለህ?
15
እኔ ከልጅነቴ ጀምሮ ችግረኛና ለሞት የተቃረብሁ ነበርሁ፤ መዓትህ አሠቃየኝ፤ ግራም ተጋባሁ።
16
ቍጣህ በላዬ ላይ ተከነበለ፤ መዓትህም አጠፋኝ።
17
ቀኑን ሙሉ እንደ ጐርፍ ከበቡኝ፤ በአንድነትም ዙሪያዬን ዐጥረው ያዙኝ።
18
ወዳጄንና ባልንጀራዬን ከእኔ አራቅህ፤ ጓደኛዬ ጨለማ ብቻ ሆኖ ቀረ።
← Chapter 87
Chapter 89 →