bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Psalms 86
Psalms 86
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
እግዚአብሔር ሆይ፤ ጆሮህን ወደ እኔ ጣል፤ ስማኝም፤ እኔ ድኻና ችግረኛ ነኝና።
2
ለአንተ የተለየሁ ሰው ነኝና ነፍሴን ጠብቃት፤ አንተ አምላኬ ሆይ፤ በአንተ የታመነብህን ባሪያህን አድን።
3
ጌታ ሆይ፤ ማረኝ፤ ቀኑን ሙሉ ወደ አንተ እጮኻለሁና።
4
የባሪያህን ነፍስ ደስ አሰኛት፤ ጌታ ሆይ፤ ነፍሴን ወደ አንተ አነሣለሁና።
5
ጌታ ሆይ፤ አንተ ቸርና ይቅር ባይ ነህ፤ ለሚጠሩህ ሁሉ ምሕረትህ ወሰን የለውም።
6
እግዚአብሔር ሆይ፤ ጸሎቴን አድምጥ፤ የልመናዬን ጩኸት ስማ።
7
አንተ ስለምትመልስልኝ፣ በመከራዬ ቀን ወደ አንተ እጣራለሁ።
8
ጌታ ሆይ፤ ከአማልክት መካከል እንደ አንተ ያለ የለም፤ ከአንተም ሥራ ጋር የሚወዳደር ሥራ የለም።
9
ጌታ ሆይ፤ አንተ የሠራሃቸው ሕዝቦች ሁሉ፣ መጥተው በፊትህ ይሰግዳሉ፤ ለስምህም ክብር ይሰጣሉ፤
10
አንተ ታላቅ ነህና፤ ታምራትም ትሠራለህ፤ አንተ ብቻህን አምላክ ነህ።
11
እግዚአብሔር ሆይ፤ መንገድህን አስተምረኝ፤ በእውነትህም እሄዳለሁ፤ ስምህን እፈራ ዘንድ፣ ያልተከፋፈለ ልብ ስጠኝ።
12
ጌታ አምላኬ ሆይ፤ በፍጹም ልቤ አመሰግንሃለሁ፤ ስምህንም ለዘላለም አከብራለሁ፤
13
ለእኔ ያሳየሃት ምሕረት ታላቅ ናትና፤ ነፍሴንም ከሲኦል ጥልቀት አውጥተሃል።
14
አምላክ ሆይ፤ እብሪተኞች ተነሥተውብኛል፤ የዐመፀኞችም ጉባኤ ነፍሴን ይሿታል፤ አንተንም ከምንም አልቈጠሩም።
15
ጌታ ሆይ፤ አንተ ግን መሓሪና ርኅሩኅ አምላክ ነህ፤ ለቍጣ የዘገየህ፣ ምሕረትህና ታማኝነትህ የበዛ።
16
ወደ እኔ ተመልከት፤ ማረኝም፤ ለባሪያህ ኀይልህን ስጥ፤ የሴት ባሪያህንም ልጅ አድን።
17
የሚጠሉኝ አይተው ያፍሩ ዘንድ፣ የበጎነትህን ምልክት አሳየኝ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ረድተኸኛልና፤ አጽናንተኸኛልም።
← Chapter 85
Chapter 87 →