bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Psalms 79
Psalms 79
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
አምላክ ሆይ፤ ሕዝቦች ርስትህን ወረሩ፤ የተቀደሰውን ቤተ መቅደስህን አረከሱ፤ ኢየሩሳሌምንም አፈራርሰው ጣሏት።
2
የባሪያዎችህን ሬሳ ለሰማይ ወፎች፣ የቅዱሳንህንም ሥጋ ለምድር አራዊት፣ ምግብ አድርገው ሰጡ።
3
ደማቸውንም በኢየሩሳሌም ዙሪያ፣ እንደ ውሃ አፈሰሱ፤ የሚቀብራቸውም አልተገኘም።
4
እኛም ለጎረቤቶቻችን መዘባበቻ፣ በዙሪያችንም ላሉት መሣቂያ መሣለቂያ ሆንን።
5
እግዚአብሔር ሆይ፤ ይህ እስከ መቼ ነው? የምትቈጣውስ ለዘላለም ነውን? ቅናትህስ እንደ እሳት ሲነድድ ይኖራልን?
6
በማያውቁህ ሕዝቦች ላይ፣ ስምህን በማይጠሩ፣ መንግሥታት ላይ፣ መዓትህን አፍስስ፤
7
ያዕቆብን በልተውታልና፤ መኖሪያ ቦታውንም ባድማ አድርገዋል።
8
የአባቶቻችንን ኀጢአት በእኛ ላይ አትቍጠርብን፤ ምሕረትህ ፈጥና ወደ እኛ ትምጣ፤ በጭንቅ ላይ እንገኛለንና።
9
አዳኛችን የሆንህ አምላክ ሆይ፤ ስለ ስምህ ክብር ብለህ ርዳን፤ ስለ ስምህ ስትል፣ ታደገን፤ ኀጢአታችንንም ይቅር በል።
10
ሕዝቦች፣ “አምላካቸው የት አለ?” ለምን ይበሉ? የፈሰሰውን የአገልጋዮችህን ደም በቀል፣ ዐይናችን እያየ ሕዝቦች ይወቁት።
11
የእስረኞች ሰቈቃ በፊትህ ይድረስ፤ በክንድህም ብርታት፣ ሞት የተፈረደባቸውን አድን።
12
ጌታ ሆይ፤ ጎረቤቶቻችን በአንተ ላይ የተዘባበቱትን መዘባበት፣ ሰባት ዕጥፍ አድርገህ አስታቅፋቸው።
13
እኛ ሕዝብህ፣ የማሰማሪያህ በጎችህ፣ ለዘላለም ምስጋና እናቀርብልሃለን፤ ከትውልድ እስከ ትውልድም፣ ውለታህን እንናገራለን።
← Chapter 78
Chapter 80 →