bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Psalms 6
Psalms 6
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
እግዚአብሔር ሆይ፤ በቍጣህ አትገሥጸኝ፤ በመዓትህም አትቅጣኝ።
2
እግዚአብሔር ሆይ፤ ዐቅመ ቢስ ነኝና ማረኝ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ ዐጥንቶቼ ተናግተዋልና ፈውሰኝ።
3
ነፍሴ እጅግ ታውካለች፤ እስከ መቼ፣ አንተ እግዚአብሔር ሆይ፤ ይህ እስከ መቼ ድረስ ይሆናል?
4
እግዚአብሔር ሆይ፤ ተመለስና ሕይወቴን ታደጋት፤ ስለ ጽኑ ፍቅርህም አድነኝ፤
5
በሞት የሚያስታውስህ የለምና፤ በሲኦልስ ማን ያመሰግንሃል?
6
ከመቃተቴ የተነሣ ዝያለሁ፤ ሌሊቱን ሁሉ በልቅሶ ዐልጋዬን አርሳለሁ፤ መኝታዬንም በእንባዬ አሾቃለሁ።
7
ዐይኖቼ በሐዘን ብዛት ደክመዋል፤ ከጠላቶቼም ሁሉ የተነሣ ማየት ተስኗቸዋል።
8
እናንተ ክፉ አድራጊዎች ሁሉ፤ ከእኔ ራቁ፤ እግዚአብሔር የልቅሶዬን ድምፅ ሰምቷልና።
9
እግዚአብሔር ልመናዬን አድምጧል፤ እግዚአብሔር ጸሎቴን ይቀበላል።
10
ጠላቶቼ ሁሉ ያፍራሉ፤ እጅግም ይደነግጣሉ፤ በመጡበት ይመለሳሉ፤ ድንገትም ይዋረዳሉ።
← Chapter 5
Chapter 7 →