bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Psalms 50
Psalms 50
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
ኀያሉ አምላክ፣ እግዚአብሔር ተናገረ፤ ከፀሓይ መውጫ እስከ ፀሓይ መግቢያ ድረስ ምድርን ጠራት።
2
ፍጹም ውብ ከሆነችው ከጽዮን፣ እግዚአብሔር አበራ።
3
አምላካችን ይመጣል፤ ዝምም አይልም፤ የሚባላ እሳት በፊቱ፣ የሚያስፈራ ዐውሎ ነፋስም በዙሪያው አለ።
4
በሕዝቡ ይፈርድ ዘንድ፣ በላይ ያለውን ሰማይንና ምድርን እንዲህ ብሎ ይጠራል፤
5
“በመሥዋዕት ከእኔ ጋር ኪዳን የገቡትን፣ ቅዱሳኔን ወደ እኔ ሰብስቧቸው።”
6
ሰማያት ጽድቁን ያውጃሉ፤ እግዚአብሔር ራሱ ፈራጅ ነውና።
7
“ሕዝቤ ሆይ፤ ስማኝ፤ ልንገርህ፤ እስራኤል ሆይ፤ በአንተ ላይ ልመስክር፤ አምላክህ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።
8
ስለ መሥዋዕትህ አልነቀፍሁህም፤ የሚቃጠል መሥዋዕትህማ ሁልጊዜ በፊቴ ነው።
9
እኔ ግን ኰርማህን ከበረት፣ ፍየሎችህንም ከጕረኖ የምፈልግ አይደለሁም፤
10
የዱር አራዊት ሁሉ፣ በሺሕ ተራራዎች ላይ ያለውም እንስሳ የእኔ ነውና።
11
በየተራራው ያለውን ወፍ ሁሉ ዐውቃለሁ፤ በሜዳ የሚገኘው ተንቀሳቃሽ ፍጡር ሁሉ የእኔ ነው።
12
ብራብ ለአንተ አልነግርህም፤ ዓለምና በውስጧ ያለውም ሁሉ የእኔ ነውና።
13
ለመሆኑ፣ እኔ የኰርማ ሥጋ እበላለሁን? የፍየልንስ ደም እጠጣለሁን?
14
ለእግዚአብሔር የምስጋና መሥዋዕት አቅርብ፤ ለልዑልም ስእለትህን ስጥ።
15
በመከራ ጊዜ ወደ እኔ ጩኽ፤ አድንሃለሁ፤ አንተም ታከብረኛለህ።”
16
ክፉውን ግን እግዚአብሔር እንዲህ ይለዋል፤ “ሕጌን ለማነብነብ፣ ኪዳኔንም በአፍህ ለመናገር ምን መብት አለህ?
17
ተግሣጼን ትጠላለህና፤ ቃሌንም ወደ ኋላህ ትጥላለህ።
18
ሌባውን ስታይ አብረኸው ነጐድህ፤ ዕድል ፈንታህንም ከአመንዝሮች ጋር አደረግህ።
19
አፍህን ለክፋት አዋልህ፤ አንደበትህም ሽንገላን ጐነጐነ።
20
ተቀምጠህ ወንድምህን አማኸው፤ የእናትህንም ልጅ ስም አጐደፍህ።
21
ይህን አድርገህ ዝም አልሁ፤ እንደ አንተ የሆንሁ መሰለህ። አሁን ግን እገሥጽሃለሁ፣ ፊት ለፊትም እወቅሥሃለሁ።
22
“እናንተ እግዚአብሔርን የምትረሱ፤ ይህን ልብ በሉ፤ አለዚያ ብትንትናችሁን አወጣለሁ፤ የሚያድናችሁም የለም።
23
የምስጋናን መሥዋዕት የሚሠዋ ያከብረኛል፤ መንገዱንም ቀና ለሚያደርግ ፣ የእግዚአብሔርን ማዳን አሳየዋለሁ።”
← Chapter 49
Chapter 51 →