bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Psalms 47
Psalms 47
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
ሕዝቦች ሁላችሁ እጆቻችሁን አጨብጭቡ፤ ድምፃችሁን ከፍ አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር እልል በሉ።
2
በምድር ሁሉ ላይ ታላቅ የሆነው ንጉሥ፣ ልዑል እግዚአብሔር የሚያስፈራ ነውና።
3
ሕዝቦችን ከእኛ በታች አደረገ፤ መንግሥታትንም ከእግራችን ሥር አስገዛልን።
4
ለሚወድደው ለያዕቆብ ክብር የሆነችውን፣ ርስታችንን እርሱ መረጠልን።
5
አምላክ በእልልታ፣ እግዚአብሔር በመለከት ድምፅ ዐረገ።
6
አምላካችንን አወድሱት፤ አወድሱት፤ ንጉሣችንን አወድሱት፤ አወድሱት፤
7
እግዚአብሔር የምድር ሁሉ ንጉሥ ነውና፤ ምርጥ ዝማሬ አቅርቡለት።
8
እግዚአብሔር በሕዝቦች ላይ ነግሧል፤ እግዚአብሔር በተቀደሰ ዙፋኑ ላይ ተቀምጧል።
9
ከአብርሃም አምላክ ሕዝብ ጋር፣ የሕዝቦች መኳንንት ተሰበሰቡ፤ የምድር ነገሥታት የእግዚአብሔር ናቸውና፤ እርሱም እጅግ ከፍ ከፍ ያለ ነው።
← Chapter 46
Chapter 48 →