bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Psalms 41
Psalms 41
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
ለድኾች የሚያስብ ሰው ምስጉን ነው፤ እርሱንም እግዚአብሔር በክፉ ቀን ይታደገዋል።
2
እግዚአብሔር ይጠብቀዋል፤ በሕይወትም ያኖረዋል፤ በምድርም ላይ ይባርከዋል፤ ለጠላቶቹም ምኞት አሳልፎ አይሰጠውም።
3
ታሞ ባለበት ዐልጋ ላይ እግዚአብሔር ይንከባከበዋል፤ በበሽታውም ጊዜ መኝታውን ያነጥፍለታል።
4
እኔም፣ “ እግዚአብሔር ሆይ፤ ምሕረት አድርግልኝ፤ አንተን በድያለሁና ነፍሴን ፈውሳት” አልሁ።
5
ጠላቶቼ በክፋት በመናገር፣ “የሚሞተው መቼ ነው? ስሙስ የሚደመሰሰው ምን ቀን ነው?” ይላሉ።
6
ሊጠይቀኝ የሚመጣ ቢኖር፣ በልቡ ስድብ እያጠራቀመ፣ ከዐንገት በላይ ይናገራል፤ ወጥቶም ወሬ ይነዛል።
7
ጠላቶቼ ሁሉ ግንባር ፈጥረው ይንሾካሾኩብኛል፤ እንዲህ እያሉም፣ የከፋ ነገር በላዬ ያውጠነጥናሉ፤
8
“ክፉ ደዌ ይዞታል፤ ከእንግዲህም ከተኛበት አይነሣም።”
9
እንጀራዬን ተካፍሎኝ የበላ፣ የምተማመንበትም የቅርብ ወዳጄ፣ በእኔ ላይ ተረከዙን አነሣ።
10
እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ግን ምሕረት አድርግልኝ፤ የእጃቸውን እንድከፍላቸው አስነሣኝ።
11
ጠላቴ በላዬ ድል አላገኘምና፣ እንደ ወደድኸኝ በዚህ ዐወቅሁ።
12
ስለ ጭንቀቴ ደግፈህ ይዘኸኛል፤ በፊትህም ለዘላለም ታኖረኛለህ።
13
የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ፣ ከዘላለም እስከ ዘላለም የተባረከ ይሁን፤ አሜን፤ አሜን።
← Chapter 40
Chapter 42 →